እግዚአብሔር የሚናገረውን ተቀበል እንጂ አትቃወመው

እግዚአብሔር የሚናገረውን ተቀበል እንጂ አትቃወመው

«… አቤቱ፥ መርምረኝ ልቤንም እወቅ፤ ፍተነኝ መንገዴንም እወቅ፤ በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ፤ የዘላለምንም መንገድ ምራኝ»(መዝ. 139፡23 – 24)።

ብዙውን ጊዜ እኛ በኃጢአታችን ስንወቀስ እግዚአብሔር ከፊታችን ቆሞ ስለሚገዳደረን ነጭናጫዎች እንሆናለን። ኃጢአታችን (ጥፋታችን) አምነን አስቀምንቀበል፣ ከእርሱም (ከኃጢአታችን) ለመመለስ የተዘጋጀን እስከምንሆን፣ ይቅርታ እስከምንጠይቅ ድረስ ደስተኛ ልንሆን የማንችልበት የስሜት ግፊት ይሰማናል። ከእግዚአብሔር ጋር ወደ መስማማት በመጣንበት በዚያው ጊዜ ውስጥ የእኛ ሰላም ይመለስና ባህርያችንም ወደ መሻሻል ይመጣል።

ሰይጣን በመኮነንና በማሳፈር እኛ በጸሎት በድፍረት ወደ እግዚእበሔር እንዳንቀርብ ሊያግደን ሲል ይዋጋናል። ምክንያቱም ፍላጎታችን በእርሱ (በእግዚአብሔር) ይሟላልና ከእግዚአብሔር ጋር በምናደርገው ህብረት ተመልሰን ደስተኛ እንሆናለንና። ስለራሳችን ክፉ ስሜት የሚሰማንና እግዚአብሔር እኛን እንደሚቀጣን የምናስብ ከሆነ ይህ ከእርሱ ህልውና እኛን ይለየናል። እርሱ ፈጽሞ አይተወንም። ነገር ግን ፍርሃት በእርሱ ህልውና ውስጥ እንዳንኖር ያደርገናል።

በወቀሳና በኩነኔ መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ እጅግ ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት ማወቅና እውነትን ለይቶ ማወቅ ያስፈለገበት ምክንያት ለዚሁ ነው። በኃጢአት የሚመጣውን ወቀሳ ብንጠብቅና ህይወታችን ከፍ ይላል እንዲሁም ከኃጢአት ነጻ እንሆናለን። ኩነኔ ግን የሚያደርገው ስለራስህ መጥፎ ስሜት እንዲሰማህና አብዛኛውን ጊዜ ወደ ባሰ ክፋት የሚመራህ የችግር መንስኤ ይሆናል።

ስትጸልይ እግዚአብሔርን በመደበኛነት እንዲናገርህና በኃጢአትህ አንተን እንዲወቅስህ ጸልይ።የእርሱ ወቀሳ በረከት እንጂ ችግር እንዳይደለ አረጋግጥ። የጸሎት ጊዜዬን ስጀምር ሁልጊዜ ማለት ይቻላል የሰማዩን አባቴን የሠራሁትን አንዳች ስህተት ነገር ካለ እንዲገልጥልኝና ከኃጢአቴና ከዓመጻዬ እንዲያነጻኝ እጠይቀዋለሁ። ከእግዚአብሔር ጋር በትክክል ለትክክል ለመራመድ የኃጢአት ወቀሳ በጣም ወሳኝና አስፈላጊ ነው። የኃጢአት ወቀሳ ስጦታ አንዱ እግዚአብሔርን የምንሰማበት መንገድ ነው። ለኩነኔ የአዕምሮህን በር በመክፈት ስህተት እንዳትሠራ ነገር ግን ወደ አዲስ የነጻነት ሥፍራና ከእግዚአብሔር ወደ መጣበቅ ያመጣህ ዘንድ የተዘጋጀህ ሁን። ስለዚህ ተቀበለው እንጂ አትቃወመው።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ እግዚአብሔር ካለህበት ወደ ከፍታ ያወጣህ ዘንድ የተዘጋጀህ ሁን።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon