
«…ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው፤ ልብስዋ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው» (መዝ.45፡13)።
በጌታችን የልደት በዓል ወቅት ብዙ ጊዜ የተለያዩ መደብሮች መስኮቶች ደማቅ ሆነው የሚያብረቀርቁና በተያያዙ ውብ ስጦታዎች ተሞልተው ይታያሉ። እነዚህ ስጦታዎች እጅግ አስፈላጊ ሆነው ሊታዩ ይችላሉ። ነገር ግን ዕቃዎቹን ስንከፍታቸው ግን ከውስጥ ምንም ላናገኝባቸው እንችላለን። እነዚህ ነገሮች ለውጪ «ታይታ» እንጂ ባዶ ነገሮች ናቸው። ህይወታችንም እንዲሁ ተመሳሳይ ነው። በውጪ በሚያምር መጠቅለያ የተጠቀለለ በውስጥ ምንም ዋጋ የሌለው ነው። በሌላ በኩል ህይወታችን ከውጪ ሲታይ የሚስብና እነዲሁም ለሌሎች የሚያስቀና መስሎ ሊታይ ይችላል። ነገር ግን በውጪያዊው ማንነታችን ደረቅና ምንም የሌለው ሊሆኑ ይችላል። ውጪያዊው ህይወታችን መንፈሳዊ መስሎ ሊታይ ይችላል። ነገር ግን ልባችን ለመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ለመሆን እስካልፈቀድንለት በስተቀር ውስጣችን ምንም ኃይል የሌለው ይሆናል።
የዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ የንባብ ክፍላችን የሚያተኩረው የውስጣዊ ህይወታችን አስፈላጊነት (ጠቀሜታ) ላይ ነው። እግዚአብሔር በውስጣዊ ማንነታችን ማለትም በአመለካከታች ላይ፣ ለአንድ ነገር በምንሰጠው ምላሽ ላይ፣ በውስጣዊ መነሳሳታችን ላይ፣ ቅድሚያ በምንሰጠው ጉዳይ ላይ፣ እንዲሁም በሌሎች አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ ላይ በውስጣችን በመሆን እንዲሠራ መንፈስ ቅዱስን በውስጣችን አኖረ። በዋናነት ማንነታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ጌታነት እንደተገዛን እርሱ ሲናገረን በህይወታችን ይሰማናል። እንዲሁም የእርሱ ጽድቅ፣ ሰላምና ደስታ በመለማመድ ከውስጣችን በሚፈልቅ ለተትረፈረፈ ህይወት ኃይልን ይሞላናል (ሮሜ 14፡17)።
መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን በመኖር ክርስቶስን ይበልጥ እየመሰልን እንድንሄድ በማድረግና በእርሱ ህልውናና ምሪት ይሞላናል። ከዚያም ለሌሎች የምናካፍለው አንድ ነገር ከውስጣዊው የጠለቀ ማንነታችን ኃይለኛና ለምናገኛቸው ማንኛውም ዓይነት ሰዎች ህይወትን የሚሠጥ ነገር እንድናካፍል ከውስጣችን ይፈልቃል።
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ከውጪያዊው ህይወትህ ይልቅ በውስጣዊው ህይወትህ ላይ አተኩር።