ወሳኝ ሁን

ከሁሉም በላይ ወንድሞቼ ሆይ፤ በሰማይ ወይም በምድር ወይም በማናቸውም ነገር ቢሆን አትማሉ፤ “አዎ” ቢሆን አዎ ይሁን፤ “አይደለም” ቢሆን አይደለም ይሁን፤ ያለዚያ ይፈረድባችኋል፡፡ – ያዕቆብ 5፡ 12

ሳኝ አለመሆን አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ የቀላል ሕይወት ፍሬም አይደለም፡፡ ሀዋሪያው ያዕቆም  በሁለት አሳብ ያለ ሰው በመንገዱ እንደማይሳካላት ይናገራል፡፡   የተሳሳተ ውሳኔ ልወስን እችላለሁ በሚል ፍርሃት ሳቢያ ወሳኝ አለመሆን የትም አያደርሰንም፡፡  በቶሎ ውሳኔ ላይ ካለመድረሳችን የተነሳ ምን ያህል ጊዜ አባክነን ይሆን?

ከፊታችን ከቀረቡልን ምርጫዎች አንዱን መወሰን ሲኖርብን የትኛውን ልመረጥ ብለን ስንጣጣር እንቆማለን፡፡  ይህ ቀላል ምሳሌ ነው፡- ነገር ግን  ማሰብ ይኖርብናል፡፡  ማለዳ ላይ ከመልበሻ ቁምሳጥናችን ፊት ቆም ብለን ልብሳችንን ስንመለከት እና የሆነ ልብስ መርጠን ከዚያም እንልበስ ፤  ይህንኛውን ልልበስ ወይስ የትኛውን በሚል ከስራ ሰዐት ላይ ማረፈድ አንፈልግም፡፡

በዚህ ላበረታታችሁ እፈልጋለሁ ስለ ምርጫዎቹ ሳትጨነቁ ወይም በማመንታት ውሳኔ ከመወሰድ እንዳትገደቡ፡፡  በሁለት ሀሳብ አታመንቱ ፤ምክንያቱም ከወሰናችሁ በኋላ ውሳኔአቹን መጠራጠር ደስታችሁን ይሰርቀዋል ከምታደርጉት ነገር ሁሉ። በምትችሉት ደረጃ መልካም ውሳኔን አድርጉ በውጤቱም እግዚአብሔር ታመኑ፡፡

 ጸሎት ማስጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ  ወሳኝ አለመሆን የትም እንደማያደረሰኝ ስላሳየኸኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ይሁን ያልኩት እንዲሆን ፤ አይሆንም ያልኩት እንዲቀር እርዳኝ ፡፡  መውሰድ ያለብኝን እርምጃ ስወስድ እንደማልሳሳት  ወጤቱም ያማረ እንደሚሆን በአንተ አምናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon