የልሳናት ሥጦታዎች

የልሳናት ሥጦታዎች

ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል… ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር…. 1ኛ ቆሮ 12÷5፣ 10

የክርስቶስ አካል የሆኑ አማኞች በተወሰነ መልኩ በመንፈስ ቅዱስ ሥጦታዎች ምናልባት ከሌሎች መንፈሳዊ ልምምዶች በላይ ሲሰሩበት ይታወቃል፡፡ አንዳንድ የቤተክርስቲያን ኅብረቶች ስለመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ስለመንፈስ ቅዱስ ሥጦታዎች በተከታታይ ሲያስተምሩና የፀጋውንም አሰራር ሲከታተሉ ሌሎች ግን በጉዳዩ ላይ እያስተማሩም ደግሞ በዚህ ዘመን ላሉ ክርስቲያኖች ዘንድ እንደሚገኝም አያምኑም፡፡ እነዚህ የፀጋ ሥጦታዎች በግልፅ ያለና የመጽሐፍ ቅዱስም አንዱ ክፍል ስለሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ ባመኑ አማኞች ልጠና እና ልፈለግ የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

በአዲስ ቋንቋ መናገር መንፈሳዊ ቋንቋ መናገር ነው፡፡ ለአንዱ እግዚአብሔር ብቻ የሚገባው ነገር ግን ተናጋሪውና ሌሎች ምናልባት የማይገባቸው ሊሆን ይችላል፡፡ በግል ፀሎትና ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ኅብርትና ጥብቅ የሆነ ኅብረትን ለመፍጠር ጠቀሜታ አለው፡፡ ነገር ግን ከመንፈሳዊ ፀጋ ሥጦታ ትርጉም ጋር አብሮ መሄድ አለበት ነው፡፡ (1 ቆሮ 14÷2፣ 27-28 ተመልከት) የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ሥጦታ ችላ ማለት በጊዜው የሚፈፀመውን የፀጋ ሥጦታዎች የመለማመድ በርን በመዝጋት ሊጎዳ ይችላል፡፡ እንዲሁም ደግሞ ሰዎች በየቀኑ የእለት ኑሮአቸው የሚፈልጉትን ቁጥር ሥፍር የሌላቸውን በረከቶች በእርሱ ላይ በሮችን በመዝጋት ተስፋ ያስቆርጣቸዋል፡፡

እኔም እንደ ጳውሎስ 1 ቆሮ 14÷18 ላይ እንደተናገረው ማለት የምፈልገው በልሳናት ስለምናገር ደስ ይለኛል፡፡ ደግሞም አምላኬን አመሰግናለሁ፡፡ በብዛት በልሳናት እናገራለሁ፡፡ ምክንያቱም በመንፈሳዊ ሕይወቴ ያበረታኛል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ያለኝን ግንኙነት ይጨምርልኛል፡፡ የእርሱን ድምፅ በግልፅ እንድሰማ ያስችለኛል፡፡ ጳውሎስ በግልፅነት በልሳናት ይናገራል፡፡ መቶ ሃያዎቹ ደቀመዛሙርት በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉት ሁላቸውም በሌላ ልሳናት ተናግረዋል፡፡ ሌሎችም አማኞችም በመንፈስ ቅዱስ የተጠመቁት በሐዋሪያት ሥራ መጽሐፍት እንደተዘገበው አንሳተፍም፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- ለመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ሥጦታ ክፍት በመሆን አዳዲስ ነገሮችን ለመማር እንድትችል የተዘጋ አእምሮ አይኑርህ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon