የእግዚአብሔር የልቡ ሃሣብ

የእግዚአብሔር የልቡ ሃሣብ

“የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘለዓለም ይኖራል፡፡ የልቡም አሳብ ለልጅ ልጅ ነው፡፡ መዝ 33÷11

በየቀኑ ከእግዚአብሔር ለመስማት እንደምትፈልግ አውቃለሁ፡፡ እኔም ይሄን በቅንነት እንደሚቻል አምናለሁ አንተ የመስማት ልማድህን ካዳበርክ ትችላለህ፡፡ የእርሱ የእግዚአብሔር ምክር ለትውልድ ሁሉ የሚገኝ ነው፡፡ ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ ጊዜ የወስዱ ናችው፡፡ እግዚአብሔርን መጠበቅ ማለት ለሰዓታት ቁጭ ብሎ ከእርሱ ለመስማት መሞከር ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ያለ እርሱ ምንም ትክክል የሆነ ነገር መስራት እንደማንችል እውቅና መስጠት ማለት ነው፡፡ በሥጋችን ኃይል በመሮጥ የምንፈልገውን ነገሮች ማድረግ የለብንም፡፡ ነገር ግን ለእርሱ ምርትና አመራር መጠየቅ አለብን፡፡

እኔ በሕይወቴ እግዚአብሔር እንዲመራኝ ስጠይቀው እንደሚመራኝ እታመነዋለሁ፡፡ በዕለት ጉዞዬን እንቅስቃሴዬ ውስጥ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንድነግረኝ የእግዚአብሔርን የጎላ ድምፅ በጆሮዬ እየሰማው አይደለም የምራመደው፡፡ ነገር ግን የውስጥ የልብ ምስክርነት በማረጋጥ ማለዳ በግሌ የቀኑን ዕቅድ ይዤ እነቃለሁ፡፡ ልጄ ለምሣ ግብዣ ቢጠራንም በውስጤ ከሚሰማኝ ድምፅ የተነሳ ከጌታ ጋር ጊዜ በመውሰድ ባሳልፍ እንደሚሻል ከተሰማኝ ያንኑ አደርጋለሁ፡፡ እግዚአብሔር የልቤን የውስጥ ሃሳብ ሲለውጥ ቀኔ መልካም የሚሆነው የእርሱን ምርት ከእራሴ እቅድ በላይ በማስቀደም እንደሆነ እረዳለሁ፡፡ ዛሬ እግዚአብሔር አንተን እንዲመራህ ታመን በራስህ ዕቅድ ላይ ብቻ ግትር አትሁን፡፡ እግዚአብሔር የሚያስተምርህ ነገር ወይም ሊያመልጥህ የማይገባ ነገር ለአንተ ሊኖረው ይችላል፡፡


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል: እግዚአብሔር የልብህን ሃሣብ ከለወጠ ዓላማህን ለመቀየር ታማኝ ሁን፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon