አሁንም በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደሆነ አውቀህ ዘንድ በፊትህም ሞገስን አንች ዘንድ መንገድህን እባክህ አሳየኝ፣ ይህም ሕዝብ ሕዝብህ እንደሆነ ተመልከት አለው፡፡ ዘፀ 33፡13
ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ ስትወስድ ወደ ደስተኛነት ሕይወት ለመቅብ ማረጋገጫ ነው፡፡ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ያረጋጋሃል፡፡ ጥሩ ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ማሳለፍ ማለት ጥሩ ገቢ የሚያስገኝ የልማት ሥራ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነህ እግዚአብሔር የሚደሰትበትንና የሚወደውን መለየት ትችላለህ፡፡ እንደማንኛውም ጓደኛ እንደሚደረግ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ብዙ ጊዜ ባሳለፍክ መጠን በጣም እየወደድከው ትመጣለህ፡፡
ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ ባሳለፍከው መጠን እግዚአብሔር የሚወደውን ለማወቅ በጣም ቅርብ በመሆን ለራስህም ሆነ ለሌሎች ለማመልከት ያስችልሃል፡፡ ህሊናህ ከሰዎች ጋር በምታደርገው ንግግር ውስጥ ስሜታችንን ማስቀየምህንና አለማስቀየምህን ለልብህ ስታውቅህ ፈጥነህ ወደ እግዚአብሔር በንስሃ ፀሎት እንዲህ ላሳዝነውና ላስቀይመው ፈልጌ አይደለም ልጎዳ ፈልጌ አይደለም በማለት ይቅርታ ስትጠይቅ ነገሩ ቀላል እየሆነልህ ይመጣል፡፡ ለወደፊቱም እንዲህ ዓይነት ችግሮች በሕይወትህ አይደጋገመም፡፡
እግዚአብሔር ሙሴን በእርሱ ዘንድ ሞገስ እንዳለው በገለፀለት ጊዜ (ዘፀ 33፡ 12) ሙሴ የተረዳው የእግዚአብሔር ማንኛውንም ነገር የልቡን ጥያቄና ፍላጎት መጠየቅ እንደምችል እንደገለፀለት ነው፡፡
የሙሴ ምላሽ በቀላሉ ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ኅብርት ማድረግን ነበር የጠየቀው፡፡ ሙሴ ከዚህ በፊት እግዚአብሔር በእርሱ በኩል ለትወልድ የሚተላለፍ ታሪካዊ ድንቅና ተዓምራቶች ሠርተዋል፡፡ ነገር ግን ሙሴ አሁንም የምሻው ትልቅ ፍላጎት እግዚአብሔርን በቅርበት ማወቅ ነበር፡፡
እኔ የምፀልየው የልብህ ዋና መሻት እግዚአብሔርን ማወቅ እንዲሆን ነው፡፡ እግዚአብሔርን ማወቅና መስማት በግልፅና በቅርበት በፈለከው መጠን ትችላለህ፡፡ ይህ ደግሞ የምጠይቀው ጊዜን ከእርሱ ጋር መውሰድን ነው፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንቴ፡- እግዚአብሔር አማራጮች ያ ሉትን ነገር ግን እሱ ያለው ታማኝነትን ነው፡፡