ሁሉን አዋቂ አትሁን

ሁሉን አዋቂ አትሁን

“የአምላኬ መንገድ ፍጹም ነው፥ የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፥ በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጋሻ ነው” (መዝ.18፡30)

የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል እውነት በህይወት ማዕበል ውስጥ ህይወታችን የተረጋጋ እንዲሆን ያደርጋል። እግዚአብሔር በተጻፈው ቃል በኩል የሚናገረንን ለመስማት መጠባበቅ እንችላለን። ለእኛ ያለው ዓላማው ፈጽሞ አይለወጥም ወይም አይነቃነቅም። ቃሉ ላለንበት ሁኔታ በዝርዝር በቀጥታ ባይናገረንም እንኳን የእግዚአብሔርን ሀሳብና ባህርይ እንዲሁም እርሱ ሁልጊዜ እንደሚጠነቀቅልንና መንገድሊያበጅልን እንዳለ ዋስትና እንደሚሰጠን ይናገረናል።

ቃሉ የእኛ ዕውቀት የተበታተነ፣ ሙሉ እንዳልሆነና ፍጹም እንዳይደለ ያስተምረናል። በ1ኛ ቆሮ 13።9 መሠረት እኛ የምናውቀው “በከፊል” ነው ይለናል። ይህ የሚናገረኝ በህይወታችን “እኔ ማወቅ የምፈልገውን ሁሉንም ነገር አውቃለሁ” ብለን ለመናገር መቼም ቢሆን እንደማንችል ነው። ወደ እግዚአብሔር በትህትና ቅረብና ከቃሉ ለመማር የተራብህ ሁን። በማናቸውም በሚገጥሙህ ሁኔታዎች ሁሉ ምን ማድረግ እንደሚጠበቅብህ እንዲያስተምርህ በየቀኑ በጸሎት ጠይቀው።

መንፈስ ቅዱስ በየቀኑ ወደ እውነት ሁሉ ሊመራህ እንዲችል እንደ አስተማሪህ ተቀበል (ዮሐ.16፡13 ተመልከት)። እርሱ መቼም በራስህ ልታስበው ከምትችለው በላይ የሆነ ነገሮችን ለአንተ ይገልጥልሃል። እኔ የህይወት ዘመን ተማሪ ለመሆን ወስኛለሁ፣ ለአንተም የምመክርህ ይህንኑ ነው።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ ሁሉን አዋቂ አትሁን፣ ዛሬ ከእርሱ መማር የሚገባህን እንድትማር እግዚአብሔርን ጠይቀው (ጸልይ)።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon