ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን ፈልግ

ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን ፈልግ

ኢዮሣፍጥ “ብዙ ሰዎች መጥተውብሃል” ተብሎ ተነገረው። . . ኢዮሣፍጥም ፈራ፤ እግዚአብሔርንም ለመፈለግ ወሰነ። እርሱም በይሁዳ ሁሉ ላይ ጾምን አወጀ ። (2 ዜና 20: 2-3)

ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ከእግዚአብሔር ዘንድ መስማት በፈለገበት ጊዜ በመላው የይሁዳ ግዛት ውስጥ ጾምን አወጀ። ሕዝቡ ሁሉ ይረዳቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ለመፈለግ በሙሉ ልባቸው በመናፈቅ ተሰብስው ነበር። ኢዮሳፍጥ ለእግዚአብሔር ያለውን ቅንነት እና ምን ያህል እግዚአብሔርን እንደሚፈልግ ለማሳየት ጾምን አወጀ።

ከእግዚአብሔር መስማት ከፈለግህ ጥቂት ጊዜ መመገብ እቁም እና ያንን ጊዜ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ለመውሰድ አስብ። ቴሌቪዥኑን ማጥፋት እና እሱን ከመመልከት ይልቅ ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ ማሳለፍም መጥፎ ሀሳብ አይደለም፣ እንዲሁም ከጓደኞቻቸው ጋር ከመሄድ እና ምክሮቻቸውን እና አስተያየቶቻቸውን ከመጠየቅ ይልቅ እግዚአብሔርን በመፈለግ ጥቂት ምሽቶች በቤት ውስጥ ማሳለፍም እንዲሁ። እነዚህ እና ሌሎችም ስርዓቶች ከእግዚአብሔር መስማት አስፈላጊ መሆኑን እንደተረዳህ ያረጋግጣሉ።

አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሔርን ከልባቸው የሚሹት በችግር ጊዜ ብቻ ነው፤ነገር ግን እርሱን ሁል ጊዜ አጥብቀን መፈለግ አለብን። አንድ ጊዜ እግዚአብሔር ብዙ ሰዎች ብዙ ችግርችን የሚያስተናግዱበት ምክንያት እርሱን የሚሹበት ብቸኛው ጊዜ የችግር ጊዜ ብቻ መሆኑን በመናገር እስደመመኝ። የአንዳንድ ሰዎችን ችግሮች ቢያስወግድለቸው በጭራሽ እሱን እንደማይሹ አሳየኝ። “ሁል ጊዜ ተስፋ እንደቆረጠ ሰው ፈልጊኝ ከዚያም ብዙ ጊዜ ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ራስሽን አታገኚም” አለኝ። ይህ ጥሩ ምክር ነው ብዬ አስባለሁ እናም በየቀኑ እንድትከተለው አበረታታሃለሁ።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ችግር ውስጥ እስክትሆን ድረስ አትጠብቅ፥ ሁል ጊዜ እርሱን ፈልግ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon