ለራስህ የሚሆን ቃል እወቅ

ለራስህ የሚሆን ቃል እወቅ

አባቶች ሆይ፤ ከመጀመሪያ ያለዉን እርሱን አዉቃችሁታልና፣ እጽፍላችኋለሁ፡፡ ጎበዛዝት ሆይ ብርቱዎች ስለሆናችሁ የእግዚአብሔር ቃል በእናንተ ስለሚኖር፣ ክፉዉንም ስላሸነፋችሁ፣ እጽፍላችኋለሁ፡፡ – 1 ዮሐ 2፡14

አንድ ነገር ዉስጥ ብቻ ያላችሁ መስሎአችሁ፣ በአንድም በሌላም መንገድ ችግር እየገጠማችሁና በህይወታችሁ ድል አጥታችሁ በዚህ እየተደነቃችሁ ከሆነ፤ ምናልባት በቃሉ ታዛችሁ ጊዜ ማሳለፍ ያስፈልጋችሁ ይሆናል፡፡

ብዙ ክርስቲያኖች እሁድ እሁድ ቤተ ክርስቲያን ሄደዉ አንድ ሰዉ ቃሉን ለእነርሱ ሲሰብክ ይሰማሉ ነገር ግን ቃሉን ለራሳቸዉ ፈጽሞ አያዉቁትም፡፡ የድል ሕይወት መኖር ከፈለግህ በእለት ተእለት ሕይወትህ ለእግዚአብሔር ቃል ቀዳሚዉን ሥፍራ ስጥ፡፡ ይህ በተግባራዊነት ስናወራዉ እንዲህ ሊሆንይችላል፤ በጠዋት ተነስተህ በምትዘጋጅበት ወቅት ቃሉን መናገር አሊያም ወደ ሥራህ ስትሄድ ትምህርቶችንና መዝሙሮች መስማት፣ የምሳ ሰዓትህን ቅዱስ ቃሉን ለማንበብ ወይም እየተራመድክ ለመጸልይ ልትጠቀም ትችላለህ፡፡

እነዚህ የእግዚአብሔርን ቃል ከህይወታችን ጋር ለማዋሃድ የቀረቡ ጥቂት ሀሳቦች ናቸዉ፡፡ እናንተ ለእናንተ የሚመቸዉንና በቋሚነት ልትጠቀሙት የሚትችሉበትን መንገድ ምረጡ፡፡ ለቃሉ ከፍተኛዉን ቦታ መስጠት ሕይወታችሁን ይለዉጠዋል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ! ቃልህን አንድ ሰዉ በሳምንት አንዴ እንዲነግረኝ ብቻ አልፈልግም ከሕይወቴ ጋር በሙላት ላዋህደዉ እፈልጋለሁ፡፡ ለራሴ ላዉቀዉ እፈልጋለሁ፡፡ ቃልህን በቋሚነት የምከተልበትን መንገድ አሳየኝ ምራኝም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon