መዘግየት ክህደት አይደለም

መዘግየት ክህደት አይደለም

ርስቴበእጅህነው፤ከጠላቶቼእጅናከሚያሳድዱኝአድነኝ።(መዝሙር 31:15)

ለምንጸልየዉ ጸሎት ሁልጊዜ ወዲያዉ መልስ አናገኝም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ረጅም ጊዜ መልስ መጠበቅ ሊኖረብን ይችላል፣ ይህን ስንል ግን አግዚአብሔር ጥያቄዎቻችንን አይቀበልም ማለታችን አይደለም፡፡ ስለራሳችንና ህይወታችን እግዚአብሔር ጊዜ እንዳለዉ መታመን አስፈላጊ ነዉ፡፡ ምናልባትም ጥሶ ለመዉጣት ለረጅም ጊዜ እየጸለይክ ነገርን የእግዚአበሔር ዝምታ ደግም ግራ አጋብቶህ ይሆናል፡፡ እባክህ እግዚአብሔር የግራ መጋባት ምንጭ እንዳልሆነ አስታዉስ፡፡ ይልቀስ፣ እሱ አንተን ግራ ማጋባት ሳይሆን አንተ እሱንእንድትታመነዉ እንደሚፈልግ እወቅ፡፡

መዘግየቶች ሁሉ “መለኮታዊ ናቸዉ፡፡”አብዛኛዉን ጊዜ በኛ መሰራት ያለበትን ስራ ለመስራት የጸሎታችን መልስ እግዚአብሔርንያዘገያል፡፡ በአስቸጋሪ ጊዜም እንኳ እግዚአብሔርን በታማኝነት ብናገለግል እሱን እየመሰልን እንሄዳለን፡፡ የጸሎቱን መልስ ለአስራ ሶስት አመታት የጠበቀዉን ዮሴፍን፣ ወይም ሃያ አመታት የጠበቀዉን አብርሃምን አስቡ፣ ተስፋ ቢቆርጡ ኖሮ፣ በእግዚአብሔር ላይ በመታመን የሚገኘዉን ፍሬ ማየት አይችሉም ነበር፡፡ እግዚአብሔር አይቸኩልም፣ ደግሞም አይዘገይም፡፡ አብዛኛዉ ነገሮች ከምናስበዉ በላይ ሊዘገዩ ይችላሉ፣ ከገመትናቸዉም ባለይ ሊከብዱን ይችላሉ፡፡ ነገር ግን፣ እግዚአብሔር የሚሰራዉን ነገር ሁሉ በትክክል ያዉቃል እናም የእሱን ጊዜ በመታመን እንድንጠብቅ ይፈልጋል፡፡

እግዚአብሔር ከጠላቶቻችን ሊያድነን ቃል ገብቷል፣ ነገር ግን እሱን ስንጠብቅ ለሰዉ ሁሉ መጸለይና በተቻለን መጠን ሁሉ በረከት መሆን ይገባናል፡፡ እሱን ስትጠብቅ እግዚአብሔር ስራዉን ይሰራል፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡ በመጠበቅ ሰላምን ማግኘት ተለማመድ አለበለዚያ አብዛኛዉ ህይወትህ አስቸጋሪ ሊሆንብህ ይችላል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon