የጌታን መንፈስ ለመከተል ነጻነት ይኑራችሁ

የጌታን መንፈስ ለመከተል ነጻነት ይኑራችሁ

ጌታግንመንፈስነው፤የጌታምመንፈስባለበትበዚያአርነትአለ።(2ኛ ቆሮ 3:17)

ህግ አጥባቂነት በመንፈስ የሚመራ ህይወት እንዳይኖረን የሚከለክል እነደሆነ ከዚህ በፊት በዚህ መጽሃፍ ዉስጥ ያየን ቢሆንም የበለጠ ለማብራራት እፈልጋለሁ፡፡ ምክንያቱም ይህየእግዚአብሔርን ድምጽ ለመስማት ትልቅ እንቅፋት እንደሆነ እገነዘባለሁ፡፡

በእግዚአብሔር ምሪት ካልሆነ ፍጹም ደስታን መለማመድ እንደማንችል አምናለሁ፣ በእግዚአብሔር መንፈስ እየተመራን ደግሞም በተመሳሳይ ጊዜ ከህግ በታች መኖር አንችልም፡፡ በህግ የሚመራዉ አይምሯችን የሚነግረን ሁሉም ሰዉ አንድን ነገር ሁል ጊዜ በተመሳሳይ መንገድ ማድረግ እንዳለበት ነዉ፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ግን የሚመራን በግልና አብዛኛዉን ጊዜ በተለየና በአዲስ መንገድ ነዉ፡፡
የተጻፈዉ የእግዚአብሔር ቃልም እንደዚሁ ለእያንዳንዳችን የግል ትርጉም እንደማይሰጥ ይናገራል፡፡ (2ኛ ጴጥሮስ 1፡20 ተመልከቱ)፡፡ ይህ ማለት የእግዚአብሔር ቃል አንድ ነገር ላንዱ ሌላ ነገር ደግሞ ለሌላዉ አይናገርም፡፡ ለማንኛዉም ሰዉ በመንፈስቅዱስ መመራት የግል ጉዳይ ነዉ፡፡

አንድ ሰዉ የራሱ የሆነ የጤና ችግር ስላለዉ እግዚአብሔር ያንን ሰዉ ስኳር እንዳይበላ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ይህ ማለት ሁሉም ሰዉ ሁሉ ስኳር መብላት የለበትም ማለት አይደለም፡፡ ህግ አጥባቂ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ለአንድ ሰዉ ወስደዉ ለእሱ የተሰጠ ህግ አድረገዉ ይሰጡታል፡፡

ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ ፣ ጻፎችና ፈሪሳዉያን አስርቱን ትእዛዛት ወደ ሁለት ሺ ህጎች እንደቀየሩና ሰዎች እንዲከተሏቸዉ እንዳደረጉ አንድ ጊዜ ሰማሁ፡፡ አስቡት፣እንደዚህ አይነቱን ህግ፡፡ ይህ እስራት ነዉ!
ኢየሱስ የታሰሩትን ነጻ ሊያወጣ መጣ፡፡ የፈለግነዉን ነገር ሁሉ እንደፈለግን እንድናደርግ ነጻነት አልተሰጠንም፣ ነገር ግን ከህግ እስራት ነጻ ወጥተን ለሁሉም የተሰጠዉን መንፈስ ቅዱስን እሱ በግላችን በሚመራን መንገድ እንድንከተል ነጻነት ተሰጥቶናል፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡ መንፈስ ቅዱስ በህይወትህ መንገድህ ሁሉ እንደሚናገርህና እንደሚመራህ ታመን፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon