ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም

ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም

ሰውም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ሰው በእንጀራ ብቻ በሕይወት እንደማይኖር ያስታውቅህ ዘንድ አስጨነቀህ አስርበህም፣ አንተን ያላወቅኸውን አባቶችህም ያላወቁትን መና አበላ፡፡ ዘዳ 8÷3

የእኔ አገልግሎት እኔ እንደምፈልገው ሳያድግ በፊት እናደድና ተስፋ እቆርጥ ነበር፡፡ እፀልያለሁ፣ እፆማለሁ፣ ሁሉን ነገር ለማድረግ እሞክር የማውቀውን ሁሉ በማድረግ ብዙ ሰዎች ወደ ስብሰባ (ኮንፍራንስ) እንደሚዘጋጅ እንዲመጡ እጥራለሁ፡፡

እግዚአብሔር እኔ የምፈልገውን እድገት ሳየሰጠኝ ስቀር እሟገትና አለመረጋጋት በሕይወቴ አጋጥሞኝ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ እግዚአብሔር ሁልጊዜ እኔ ከምፈልገው በታች የሰው ቁጥር በስብሰባ እንዲገኙ በማድረግ ባለኝ ብርቱ ፍላጎትና ጉጉት እንዲፈተን ያደርገኛል፡፡ እነዚያን ስብሰባዎች ለቅቄ ስወጣ እግዚአብሔር ሆይ ምን ስህተት ሠርቻለሁ; ለምንድን ነው የማትባርከኝ; እፆማለሁ፣ እፀልያለሁ፣ እሰጣለሁ ደሞም አምናለሁ፣ አንተ ግን ወደ ፍላጎቴ አትመጣም፡፡ እኔ አሁን ተስፋ ቆርጫለሁ፣ እግዚአብሔር ሆይ ለምን የእኔን የፀሎት ጥያቄ አትመልስም ብዬ እጠይቃለሁ፡፡

እግዚአብሔር ‹‹ጆሲ እኔ ሰው በእንጀራ ብቻ እንደማይኖር እያስተማርኩሽ ነው›› ብሎ ተናገረኝ፡፡ ይህንን ቃል ለእስራኤላዊያንም እንዲህ ብሎ በምድረ በዳ አቋርጦ ወደ ተስፋ ምድራቸው እየተጓዙ ባለበት ወቅት የነገራቸው፡፡ ይህ ደግሞ የታቀደው እርሱን ትሁታን ለማድረግና በእግዚአብሔር ላይ ማረፋቸውን ለማረጋገጥ ነው፡፡ እንዲሁም ሰው በእንጀራ ብቻ እንደማይኖርና ነገር ግን ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል እንደሆነ ለማስተማር ነው፡፡

እግዚአብሔር ይፈትነኛል እንዲሁም ትሁት እንዲሆን ያደርጋል ብዬ ማሰብ አልፈልግም፡፡ እግዚአብሔር ለእኔ ‹‹ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም›› ብሎ በመናገሩ እርሱ የእኔን ፍላጎትና በንፁህ ለእርሱ እንድሆን ለሌላ ለምንም ቅድሚያ እንዳይኖረኝ ለማድረግ እንደምፈልግ ተረዳው፡፡ የእኔ አገልግሎት በጊዜው አደገ፡፡ ነገር ግን በመጀመሪያ እግዚአብሔር የሕይወቴ ቀዳሚ ከህግ በኋላ፣ በእግዚአብሔር በራሱ ብቻ ስትረካ፣ ሌሎች አንተ እንዲኖርህ የምትፈልገውን ሁሉ ይሰጥሃል፡፡ እርሱ የእኛ እውነተኛ የሕይወት እንጀራና የነፍሳችን መጋቢ ነው፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- በአንተ፡- በእንጀራ ብቻ መኖርን እምቢ በል፣ እግዚአብሔርን ከሁሉ ነገር በላይ ፈልግ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon