ጠላትህን ተስፋ አስቆርጥ

ጠላትህን ተስፋ አስቆርጥ

ወንድሞቼ ሆይ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትና እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ ልዩ ልዩ ፈተና ስደርስባችሁ እንደሙሉ ደስታ ቀጠናት፡፡ ያዕ 1÷2-3

ብዙ ክርስቲያኖች ከምሳሳቱት ስህተቶ አንደኛው የሆነ ችግር ስገጥማቸው አስቸጋሪው ሁኔታ እንዲቆምላቸው ያፀልያሉ፡፡ እኔ እንደማምነው ከሆነ ግን መፀለይ ያለግን ለብርታትህ ለፅናት ነው፡፡ እግዚአብሔርን ልንጠይቅ የሚገባን ፀንተን ያለማወላወል ለመቆም መሆን አለበት፡፡ ጠላት ታላቁን የእርሱን ጠመንጃ ወደ እኛ ቢያነጣጥር የምችለውን ነገሮች ሁሉ በሕይወታችን ብገለባብጥ፣ ንግዳችን በኪሣራ ቢመታ፣ ቤተሰባችን ቢበታተን፣ ሠላማችን ቢሰረቅ እኛ ደግሞ በዚህ ሁሉ በመጽናት በትዕግስት ስንቆምና ስንቆይ ጠላት በመገረም ሁኔታ ተስፋ ይቆርጣል፡፡ ከዚያም ውሎ አድሮ ይሸነፋል፡፡ ምክንያቱም እኛ ከእርሱ ጋር ተከትለን በመጨናነቅ አንተባበረውምና ነው፡፡

በፊልጵስዮስ 1÷25 በአንድም ነገር እንኳ በተቃዋሚዎች አትደንግጡ ይህም ለእርሱ የጥፋት ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው ይላል፡፡ ይህ ጥቅስ እኛ እንዳንፈራ ወይም ሰይጣን እኛን ሲቃወመን እንዳንፈራ ነገር ግን ፀንተን እንድንቆም ያበረታታናል፡፡ ይህንን ባደረግን ጊዜ ሰይን እኛን መያዝ አለመቻሉን ብቻ ሳይሆን ለጌታም የምናመለክተው እምነት በእርሱ እንዳለ እንገልፃለን፡፡ እኛ የምናደርገው እንቅስቃሴ በእርሱ ያለንን ታማኝነት ደግሞ እግዚአብሔር ኃይሉን እንዲለቅልንና ከሁኔታዎቻችን እኛን ነፃ የሚያደርግበት ምልክት ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልገው አንተ እርሱን እንድትሰማና በፅናት ያለፍርሃት እንድትቆም እንደሆነ አምናለሁ፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- መታመኛህን በእግዚአብሔር አድርግና በጽናት ቁም ጠላትህን ተስፋ ታስቆርጣለህ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon