የተዋጣለት ፀሎት መፀለይ አይጠበቅብህም”

የተዋጣለት ፀሎት መፀለይ አይጠበቅብህም"

“ስለ እነርሱ ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል፡፡ ዕብ 7÷25

ከእግዚአብሔር ጋር ባለኝ ኅብረት በእርግጥ የሚያበረታታህን እውነት ላካፍልህ እወዳለሁ፡፡ ብዙ ሰዎች እንደሚያደርጉ ሁሉ በፀሎቴ እንደአስፈላጊነቱ ስፀልይ ሁልጊዜ ቅር የሚለኝ በፀሎቴ ውስጥ ይሰማኛል፡፡ በመጨረሻ ላይ አንድ ቀን ‹‹ለምንድን ነው ይህ ዓይነት ስሜት የሚሰማኝ;›› እኔ ሁልጊዜ እፀልያለሁ፣ በፀሎት ጥሩና በቂ ጊዜ በፀሎት አሳልፋለሁ ታዲያ ሁልጊዜ ወደ ፀሎቴ ማጠናቀቂያ አካባቢ ሲደርስ አለመርካት የሚሰማንና በፀሎቴ ወደ አንተ የደረስኩ የሚመስለኝ; በማለት እግዚአብሔርን ጠየኩ፡፡ እርሱም ‹‹አንቺ በፀሎትሽ የተዋጣለት ፀሎት እንደምትፀልይ ስለማይሰማሽ ነው፡፡ ስለራስሽ ጥርጣሬ ስላለሽ ያ ደግሞ የፀሎትሽን ኃይል እንድትጠራጠሪ ያደርግሻል፡፡

በኋላ ነገር ከእኔ የፀሎት ፍርሃቶች የሚመነጭና ከሚሰማኝ ጥርጣሬ፣ በእምነት አለመፀለይ ነው፣ ለረዥም ሰዓት አለመፀለይ ነው፡፡ ፀሎቴ የተዋጣለት አይደለም እና እኔ ለእግዚአብሔር ትክክለኛውን ነገር ለእግዚአብሔር ስለማልናገር ነው ከሚለው የመነጨ መሆኑን ተገነዘብኩ፡፡

እግዚአብሔር ይህንን ሲናገረኝ ከፍርሃትና ከጥርጣሬ ነፃ አወጣኝ፡፡ እንዲህ በማለት ‹‹ጆሲ ታውቃለሽ ትክክል ነሽ አዎ ፀሎትሽ የተዋጣለት አይደለም፡፡ አንቺ ፍጹም አይደለሽም፡፡ ለዚህም እኮ ነው ኢየሱስ የአንቺ አማላጅ የሆነልሽ ከዚህም የተነሣ ነው በኢየሱስ ስም የምትፀልዩ አለኝ፡፡

ትክክለኛ ፀሎት እንደፀለይክ ልሰማው ይችላል፣ ነገር ግን የሚበረታታ ነው፣ በእግዚብሔር ፊት ፀሎትህ በቀረበ ጊዜ እርሱ ይሰማል፡፡ ምክንያቱም አንተ የፀለይከው በኢየሱስ ስም እንጅ በራስህ ስም አይደለም፡፡ በኢየሱስ ስም ስንፀልይ ኢየሱስ የሆነውን ሁሉ ማቅረባችን ነው እንጂ እኛ የሆነውን አይደለም፡፡ ስለዚህ ፀሎታችን በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት አለው፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ኢየሱስ ለአንተ የተዋጣለትን ፀሎት እንድፀልይልህ ፍቀድለት፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon