ቀይ መብራት፣ አረንጓዴ መብራት

« … አሁን ግን ለእርሱ ለታሰርንበት ስለ ሞትን፥ ከሕግ ተፈትተናል፥ ስለዚህም በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም» (ሮሜ 7፡6)።

በህይወቴ ደስተኛ ያልሆንኩባቸው ጊዜያት ነበሩ። እንዲያውም ክርስቲያን በነበርኩበት ጊዜ ቢሆንም ክርስቲያን ያደርጋል ብዬ ያላስብኩትን ሁሉንም ነገር አደርግ ነበር። አሁን ወደ ኋላ መለስ ብዬ ስመለከተውና ለምን ደስተኛ እንዳልነበርኩ ዋናው ምክንያት ስለውስጠናው ህይወት ምንም የማውቀው ነገር እንዳልነበረ አረጋገጥኩ። የእግዚአብሔር ድምጽ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በውስጠናው ህይወት እንደሚመራኝና እንዴት እንደምሰማ አላውቅም ነበር። ወይም በአንዳንድ ነገሮች ምን ማድረግና ምን አለማድረግ እንዳለብኝ እንዴት እንደምታዘዘው አላውቅም ነበር።

አሁን በመንፈስ ቅዱስ አንዳንድ ጊዜ እንደ ትራፊክ ፖሊስ በውስጤ ይሰራል። ትክክለኛውን ነገር ሳደርግ ከእርሱ አረንጓዴ መብራት አገኛለሁ። እንዲሁም በተቃራኒው ስህተት ሳደርግ ቀይ መብራት ይበራብኛል። እራሴን በችግር ውስጥ በማገኝበት ጊዜ ነገር ግን በአንዳንድ አቅጣጫዎች ሙሉ የመሰጠት ሂደት የለኝም። በዚህ ጊዜ የማስጠንቀቂያ መብራት ይበራብኛል። ነገሮች ይበልጡን ትተን /አቁመን/ ለምሪት እግዚአብሔርን ስንጠይቅ መንፈስ ቅዱስ ለሚሰጠን ውስጣዊ ማንቂያ ይበልጥ ንቁ እንሆናለን። እርሱ በዝግታ በትንሹ ድምጽ ወይም እኔ «ማወቅ» ብዬ በምጠራው መንገድ ለእኛ ይናገራል። መኪና በምትነዳበት ጊዜ ለትራፊክ መንገድ ቀይና አርንጓዴ መብራት ትኩረት አንደምትሰጥ ሁሉ መንፈስ ቅዱስ በውስጠኛው ማንነትህ ላይ በጨዋነት ለሚናገረው ምንቂያ ትኩረት ስጥ። አረንጓዴውን መብራት ካገኘህ ወደ ፊት ቀጥልበት አንዲሁም ቀይ መብራት ከበራብህ ቁም።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ በአዲስ ግዛት /ሀገር/ በምትሄድበት /በምትሆንበት/ ጊዜ የአቅጣጫ ጠቋሚ መሳሪያውን ተጠቀም (የእግዚአብሔር የጸሎት ማንቂያ)።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon