በቃሉ መጽናት

በቃሉ መጽናት

በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። – ዮሐ 15:7

ብዙ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ የማንበብን ጥቅም ያዉቃሉ ነገር ግን በቃሉ የመጽናትን ጥቅምና ቃሉ በእነርሱ እንዲኖር መፍቀድን አይረዱም፡፡

ቃሉን ለማጥናትና በልባችን ለመያዝ የተጋን እንደሆነ ቃሉ ባስፈለገን ጊዜ ወዲያዉ ከቅዱሳት መጽሐፍት የማግኘት ዕድል ይኖረናል፡፡ ኢየሱስም ማንኛዉንም ነገር ስንፈልግ በጸሎት ስንጠይቀዉ እንደምንቀበለዉ ቃል ገብቶልናል፡፡

በቃሉ መኖርና ቃሉ በእኛ እነድኖር መፍቀድ እዉነተኛ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ያደርገናል (ዮሐ 8፡31ን ተመልከት)፣ በጸሎት ህይወታችን ሀይል ይሰጠናል በጸሎት ሐይል ስናገኝ ደግሞ በጠላታችን ላይ ሐይል እናገኛለን፡፡

በእግዚአብሄር ቃል እየኖርክ ነዉ፤ ቃሉስ በአንተ እንዲኖር እየፈቀድክ ነዉ? ይህ ካልሆነ እርምጃ እንድትወስድ አበረታታሃለሁ፡፡ ቃሉን ማንበብንና ማጥናትን ቀዳማይ ተግባርህ አድርግ፡፡ ቅዱሳት መጽሐፍትን መሸምደድ ጀምር በልብህም ቃሉን ሰዉር ከዚያም በሕይወት በሚገጥምህ ዉጊያ የታጠቅህና ለማሸነፍ የተዘጋጀህ ትሆናለህ


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ! በቃልህ ከመኖር የሚመጣ እዉነተኛ ደቀ መዝሙር መሆን እፈልጋለሁ፡፡ ቃልህን በትጋት በማንበብ እዉነትህን በልቤ ወደማኖር ምራኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon