በአንተ ውስጥ የከበረ ነገር አለ

በአንተ ውስጥ የከበረ ነገር አለ

«ነገር ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን» (2ኛቆሮ.4፡7)

ከማንኛውም በነገር ሁሉ ይልቅ እኔ የምፈልገው የእግዚአብሔርን ድምጽ በትክክል መስማትና በእርሱ ህልውና ውስጥ ሁልጊዜ ለመኖር ንቁ መሆንን ነው። እንዲሁም አንተም ይህንን መጽሐፍ ስታነብ የአንተም ፍላጎት እንደሚሆን አምናለሁ። አስቀድሜ እንደጻፍኩት ብዙ አመታት ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኜ አድርጌ ባመንኩ ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር በነበረኝ የጠበቀ ህብረት ደስተኛ አልነበርኩም። ሁልጊዜ እርሱን እፈልገዋለሁ ነገር ግን እርሱን እንዳላገኘሁት እንደከሰርኩ ይሰማኝ ነበር። አንድ ቀን በመስታወት ፊት ቆሜ ጸጉሬን እያበጠርኩ እያለሁ እግዚአብሔርን ቀለል ያለ ጥያቄ ጠየቅሁት፡ «እግዚአብሔር ሆይ ምንም እንኳን እኔ ሁልጊዜ በቀጣይነት ብፈልግህም እኔ ግን አንተን ሳላገኝ እንደከሰርኩ የሚሰማኝ ለምንድን ነው?» ወዲያውኑ በልቤ ውስጥ የእርሱን ደምጽ ሰማሁ እንዲህ የሚል «ጆይስ አንቺ የምትፈልጊው ከውጪ ነው እናም እኔ ግን የምፈለገው በውስጥሽ ነው» አሁን ይህንን ላብራራው የእግዚአብሔር ቃል እንደሚለው እርሱ በእኛ ውስጥ ይኖራል። ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ይህንን እውነት ለመረዳት አስቸጋሪ እንደሆነ አድርገው ያገኙታል። ለዛሬ የተመረጠው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የእግዚአብሔር የህልውና መዝገብ በእኛ ውስጥ እንዳለ ያስረዳናል፣ ነገር ግን ብዙዎች በክርስቶስ ኢየሱስ ያመኑ በእርሱን ህልውና ውስጥ ያለውን ደስታ አይለማመዱም ወይም ከእርሱ ጋር በቀጣይነት ህብረት አያደርጉም።

እግዚአብሔርን ለማግኘት እየሞከርኩ ነበር፣ ነገር ግን በጸጋውና በምህረቱ ውስጥ የነበረው እውነት እርሱ ወደ እኔ እንዲመጣና በእኔ ውስጥ መኖሪያ አደረገ። እንደ እግዚአብሔር ልጅነት ይህ እውነት ለአንተ ነው። እርሱ ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ይሆናል። እርሱ የአንተ ጥንካሬ፣ ሰላም፣ ደስታና እርዳታ ይሆንልሃል። ስለዚህ ሊናገርህ ይወዳል፣ በልብህ እርሱን ለመስማት ጀምር እናም እርሱ ከምታስበው በላይ ላንተ ቅርብህ ነውና እርሱን ፈልገው።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ እግዚአብሔርን ከሌላ ስፍራ አትፈልገው፣ እርሱ ከውስጥህ ነውና።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon