በአንድ ጊዜ አንድ እርምጃ

በአንድ ጊዜ አንድ እርምጃ

“እግዚአብሔርም አብራምን አለው፦ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ” (ዘፍ.12፡1)

አብረሃም እግዚአብሔር ሲመራው በእርሱ በመታመን እርምጃ መውሰድን ተማረ። የእርሱ ታሪክ የሚጀምረው ከዘፍ. 12።1 በዛሬው እለት ከመረጥነው ጥቅስ ይጀምራል። በዚህ ክፍል ልብ ማለት ያለብን እግዚአብሔር የሰጠው አንድ እርምጃ እንጂ ሁለት እርምጃ አይደለም። እርሱ በመሠረታዊነት የተናገረው የመጀመሪያውን እርምጃ ሳያሳካ ውም ሳይጨርስ ሁለተኛውን እንዲጀምር አልነበረም። ይህ በጣም ቀላል ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር እንዴት እንደሚናገር በጣም ጥልቅና መረዳትን የሚሰጥ ነው። እርሱ በአንድ ጊዜ አንድ እርምጃ እንድንወስድ መመሪያ ይሰጠናል።

ብዙ ሰዎች ሁለተኛውን፣ ሶስተኛውን፣ አራተኛውንና አምስተኛውን እርምጃዎች ሳያውቁ የመጀመሪያውን እርምጃ መውሰድ ይቃወማሉ ወይም ቸል ይላሉ። አንተም እንደነዚህ ዓይነት ሰው ከሆንክ በመጀመሪያው እርምጃ እርሱን በመታመን እርሱ በህይወትህ ያለውን ዓላማ ተረድተህ ወደ ፊት እንድትራመድ እንደሚያደርግህ ተስፋ አደርጋለሁ። ከመጀመሪያዎቹ ጥቂት እርምጃዎች በኋላ እምነትህ ያድጋል፣ ምክንያቱም ሁልጊዜ ከእያንዳንዱ እግዚአብሔር ከሚመራህና ለምትወስዳቸው እርምጃዎችህ ሥር አስተማማኝ መሠረት እንዳለ ስለምታረጋግጥ ነው።

እግዚአብሔር አብርሃምን ሁሉንም ነገሮችና ለእርሱ የሚመቹትን እያንዳንዱን ነገሮችን እንዲተውና አስቸጋሪ እርምጃ እንዲወስድ ጠየቀው። ነገር ግን እያንዳንዱ የሚወስዳቸው እርምጃዎች ለእርሱ ጥቅም እንደሆኑ ተስፋ ቃል ገባለት።

እግዚአብሔርን ስንታዘዝ እንባረካለን። እግዚአብሔር ለህይወታችን መልካም ዕቅድ አለው፤ ይህም ዕቅድ ለእኛ ጥቅም የሆነ ነው። እኛ ማድረግ ያለብን በእርሱ መመላለስ ነው … በአንድ ጊዜ የመጀመሪያውን እርምጃ መውሰድ።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ በአንድ ጊዜ የመጀመሪያ እርምጃ በመውሰድ የእግዚአብሔርን ድምጽ መታዘዝ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon