« … እግዚአብሔርም መጥቶ ቆመ፥ እንደ ቀድሞውም፦ ሳሙኤል ሳሙኤል ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም፦ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር አለው» (1ኛ ሳሙ.3፡10)።
ለዛሬ በተመረጠው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ የምንመለከተው እግዚአብሔር በሆነ ሁኔታ ውስጥ ሥራ እንዲሠራ ስላቀደው ሥራ ሳሙኤልን ሲናገረው ከምንመለከተው ክፍል የተወሰደው ነው። ሳሙኤል እየሰማው ያለው ድምጽ የእግዚአብሔር መሆኑን እስከማወቁ በፊት ለብዙ ጊዜ እርሱ ሲናገረው ነበር። ሳሙኤል በአንዴ ያረጋገጠው ነገር እግዚአብሔር እየተናገረው እንዳለና ለሚናገረው ድምጽ ሲመልስለት «እየሰማሁ ነው» አለ።
የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማት ለህይወትህ ላለው በእርሱ ዕቅድ ለመደሰት ወሳኝ ነገር ነው፤ ነገር ግንድምጹን መስማት አለመስማት የአንተ የግል ውሳኔ ነው። ማንም ሰው ስላንተ መስማት አይችልም፤ ይህንን አንተ ራስህ ለራስህ የምታደርገው ነው። እግዚአብሔር እንድትሰማው ይፈልጋል። እርሱ ፈቃዱን ትመርጥ ዘንድ በምንም አያስገድድህም፤ ነገር ግን ለእርሱ አዎን ማለት እንድትችል ሊያበረታታህ እርሱ ሁሉንም ያደርጋል ይችላልም።
እግዚአብሔር እርሱ እንድታደርግ የሚፈልገውን ነገር ታውቅ ዘንድ፣ ስለአንተ ምን እንደሚሰማው፣ ለአንተ ህይወት ያለውን እቅድ ኦንድታውቅ ይፈልጋል። ምሳ.3፡7 « … በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን፤»። በሌላ በኩል ህይወትህን በራስህ እንደምታስተዳድርና ያለእግዚእበሔር እርዳታና ምሪት ለራስህ መልካም ሥራ እንደምታደርግ ጭምር አታስብ። ብዙ በራስ መተማመን (ድፍረት) ካጎለበትህ የእርሱን ድምጽ መስማት ትችላለህ፤ የእርሱን ምሪትና አመራር ለተሻለ ህይወት ትቀባላለህ።
እግዚአብሔር ለአንተ ሊናገር ስለሚፈልግ ዛሬ እርሱ ሲናገርህ ለመስማትና ለእርሱ ድምጽ ሙሉ ትኩረትህን ለመስጠት ዛሬ ወስን።
የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡እግዚአብሔር ለህይወትህ ዓላማ አለው፤ እንድታውቀው
የሚፈልገውን ሁሉንም ነገር ለአንተ ይናገራል። አስታውስና ስማው።