እምነትህ ይሠራል

እምነትህ ይሠራል

በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ በፍቅር የምሠራ እምነት እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና፡፡ ገላ 5÷6

ብዙ ሰዎች ትልቅ እምነት የመጀመሪያ ደረጃ የመንፈሳዊነት ምልክት እንደሆነ ያስባሉ፡፡ ነገር ግን እኔ እንደማምነው ትክክለኛው የመንፈሳዊነት መመዘኛው የፍቅር ጉዞ ነው፡፡ የፍቅር ጉዞአችን እምነታችንን ያጠነክራል፡፡ በእግዚአብሔር ላይ እምነት ከሌለን ከእርሱ ጋር ጥሩ ግንኙነት አይኖረንም፡፡ ነገር ግን ፍቅር እምነታችንን ያሳያል፣ ያጠነክራል፣ እንዲሁም ይገልጣል፡፡ በእውነት እግዚአብሔርን የምንወድና በእርሱ የምናምን ከሆነ ሰዎችንም እንወዳለን፡፡

የዛሬው ጥቅስ የሚያስተምረን እምነት የሚሠራው በፍቅር እንደሆነ ነው፡፡ እናም ፍቅር ንግግር ወይ ታሪክ አይደለም፡፡ በእርግጥ መጽሐፍ ቅዱስ ወንድማችንን በችግር ውስጥ አይተን የማንረዳው ከሆነ በፍቅር እየተመላለስን አይደለም ይለናል፡፡ (1 ዮሐ. 3÷17 ተመልከት) ኢየሱስ ሁሉም ህግጋትና ነብያት የሚጠቀለሉት በፍቅር ነው ብሎ አወጀ ‹‹ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ እና በፍጹም ሃሳብህ ውደድ፡፡›› ይህ የመጀመሪያ ታላቁ ትዕዛዝ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ እንደዚህ የምትል ናት፡፡ ‹‹ባለእንጀራህን እንደራስህ ውደድ የምትል ናት፡፡ ሁሉም ህግጋትና ነብያት በእነዚህ ሁለቱ ትዕዛዞች ላይ የሚንጠለጠሉ ናቸው፡፡ (ማቴ 22÷37-40 ተመልከት) ኢየሱስ እነዚህን ቃላት የተናገረው የትኛው ትዕዛዝ ታላቅና በጣም አስፈላጊ ነው ብሎ ለጠየቁት ሰዎች ነበር፡፡ በመሠረቱ እነርሱ ያሉት ‹‹እርግጡን ንገረን›› ነው፡፡ እርሱም መለሰላቸው ‹‹እሺ እርግጠኛውን ነገር ማወቅ ፈለጋችሁ; ታዲያ እኔን ውደዱ እንዲሁም ሰዎችን ውደዱ፡፡›› ነገሩ እንዲህ ቀላል ነው፡፡ ኢየሱስ በፍቅር መመላለስ እግዚአብሔርን የሚያስደስትና የሚያከብር መንገድ እንደሆነ ሰዎች እንዲያውቁ ይፈልጋል፡፡ ካለፍቅር በእምነት መመላለስ ማለት ልክ ድንጋይ እንደሌለው ባትሪ ማለት ነው፡፡ ሁልጊዜ የፍቅር ባትሪያችን ቻርጅ ማድረጉን እርግጠኛ መሆን አለብን፡፡ አለበለዚያ የእኛ እምነት አይሠራም፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- እግዚአብሔር ፍቅር ነውና እርሱን ባወቅን መጠን ሌሎች እየወደድን እንመጣለን፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon