እምነት ምንድነው?

እምነት ምንድነው?

እንሆ ነፍሱ ኮርታለች፣ በውስጡም ቅን አይደለችም፤ ፃድቅ ግን በእምነቱ በህይወት ይኖራል፡፡ – ዕምባ 2፡4

እምነት ብዙ ጊዜ የምንጠቀመው ቃል ነው፤ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ በጣም ልናወሳስበው እንችላለን፡፡ እምነት ማለት በቀላሉ ‹‹ፍፁም የሆነ መደገፍ›› ማለት ነው፤ በሌላ አገላለፅ ታማኝነትን እና መሰጠትን ያመለክታል፡፡

እምነት ያን ያህል አካብደን ልናየው የሚገባ ትልቅና ውስብስብ ሃሳብ አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ እውነተኛ እምነት ማለት ለኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ መልዕክት ዕውቅና መስጠት ማለት ነው፡፡ ‹‹ይህ ለእኔ ትርጉም የሚሰጥ ነገር ብቻ ሳይሆን፣ ህይወቴንም በእርሱ ላይ ለመትከል ፈቃዴ ነው፡፡›› ስንል እውነተኛ እምነት የምንለው ነገር ይኖረናል ማለት ነው፡፡

መፅሐፍ ቅዱስ የማያመቻምች ፃድቅ ግን በእምነቱና በታማኝነቱ በህይወት ይኖራል ይለናል፡፡ የማያመቻምች ጻድቅ ሲባል ክርስቶስ በመስቀል ላይ በሞተው ሞት ትክክል ተደርገው የተሰሩ ሰዎችን ነው፡፡

በእምነት ትክክል ሆነን ተሰርተናል፤ እግዚአብሔርም እንደሚወደው ልጅ ነው የሚይዘን፡፡

ዛሬ ወደ እምነት መሰረቶች እንድትመለሱ አበረታታችኋለሁ፡፡ እምነታችሁን በእርሱ ላይ ስታድርጉ፣ በትክክል ትበጃላችሁ፡፡ በፍቅርና እጁን ዘርግቶ ወደእናንት የመጣውን፣ እስከማንነታችሁ ሊቀበላችሁ እና ሊወዳችሁ ዝግጁ በሆነው በእግዚአብሔር ላይ ባላችሁ እምነት ኑሩ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ! በአንተ ላይ እምነቴን ማድረግ በመቻሌ እና ‹የማያመቻምች ፃድቅ› ስለሆንኩ ዛሬ አመሰግንሃለሁ፡፡ በአንተ በእምነት እኖራለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon