እግዚአብሔር ይታደጋል

እግዚአብሔር ይታደጋል

ከአንበሳ መዳፍና ከድብ መንጋጋ ያደነኝ እግዚአብሔር አሁንም ከዚህ ፍልስጤማዊ እጅ ያድነኛል፡፡ ሳዖልም ሂድ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን አለዉ፡፡ – 1 ሳሙ 1737

ቀዉስ ጊዜ እግዚአብሔር ሊታደግ እንደሚማይችል ማሰብ ቀላል ነዉ፡፡ እምነትህን ለማጠንከር እነዚህን እግዚአብሔር ልጆቹን ከጥቃት የታደገባቸዉን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አስታዉስ፡፡

በ1ኛ ሳሙ 17፡17 ላይ ዳዊት ጎልያድን ሊገጥመዉ እንደሚችል አዉቋል ምክንያቱም ቀድሞዉኑ እግዚአብሔር ከአንበሳና ከድብ አድኖታልና፡፡

በዳንኤል 3 ላይ ስድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብድናጎ ንጉሱ ላቆመዉ ጣዖት አንሰግድም ብለዉ እግዚአብሔርን ማምለካቸዉን ቀጠሉ፡፡ ዉጤቱም ሰባት እጥፍ በሚነደዉ የእቶን እሳት ተወሰነባቸዉ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ከእቶኑም እሳት ታድጓቸዋል አልፎም አብሮአቸዉ እሳቱ ዉስጥ ነበር፡፡

የእግዚአብሔር መታደግና ፈቃደኛነት ብቁ እንደሆነ ለማየት ዳንኤል ሌላዉ ምሳሌአችን ሆኖ ያገለግላል፡፡ ወደ እግዚአብሔር በመጸለዩ በአናብስት ጉድጓድ ቢጣልም እግዚአብሔር እንደሚታደግና ጠላቶቹ እንደሚረቱ ዳንኤል ያዉቅ ነበር (ት. ዳንኤል 6ን ተመልከት)፡፡

እዚህ ያለዉን ዝንባሌ ልብ አላችሁ? የእግዚአብሔር ሰዎች እግዚአብሔር ምን እንደሚፈልግና ምን መስራት እንዳለባቸዉ አዉቀዉ በእምነት እርምጃ ሲወስዱ እግዚአብሔር ምላሽ ይሰጣል ድልም ያቀዳጃቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ከማንኛዉም ሁኔታ ዉስጥ መታደግ ይችላል፡፡ የእርሱ የመታደግ ኀይል ከችግሮቻችሁ በላይ እንደሆነ ዛሬ እወቁ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! በተለያየ ጊዜ አንተ ልጆችህን ከችግር አዉጥተሃቸዋል አሁንም አንተ አልደከምክም፡፡ አንተ ከሁኔታዎች ሁሉ በላይ ነህና አንተን አምንሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon