የመንፈሳዊ ብስለት እውነተኛ መመዘኛ

የመንፈሳዊ ብስለት እውነተኛ መመዘኛ

በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፣ በፍቅር የሚሰራ እምነት እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምም፡፡ – ገላ 5፡6

እግዚአብሔር ከምንም ነገር በላይ እውነተኛ፣ ንፁህ እና ከፍ ያለ ፍቅር ለእርሱና ለሌሎች እንዲኖረን ነው የሚፈልገው፡፡ በህይወታችን ማድረግ የምንችለው አንድ ነገር ቢኖር፣ እርሱም ሌሎችን መውደድ መሆን አለበት፡፡

ታላቅ እምነት የመንፈሳዊ ብስለት የመጀመሪያው ምልክት አድርገው የሚወስዱ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ እኔ ግን የማምነው ከዚህ የተለየ ነው፤ ለእኔ በፍቅር መመላለስ ወይም ፍቅርን በተግባር መግለፅ የመንፈሳዊ ብስለት ምርጥና እውነተኛ መለኪያ እንደሆነ ነው፤ ይህም እምነታችን እንዲንቀሳቀስ ጉልበት እንደሚሆንም አውቃለሁ፡፡

መፅሐፍ ቅዱስም የሚያስተምረን፣ እምነት የሚሰራው በፍቅር እንደሆነ ነው፡፡ ገላትያ 5፡6 ላይም እምነት የሚነቃቃውና ጉልበታም የሚሆነው እንዲሁም ራሱንም የሚገልፀውና የሚሰራው በፍቅር እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ፍቅር የሆነ የምንናገረው ነገር ወይም የሆነ ፅንሰ ሃሳብ አይደለም፤ ፍቅር ተግባር ነው፡፡

ፍቅር ሳይኖር በእምነት መንቀሳቀስ ያለባትሪ የእጅ መብራት እንደመያዝ ነው፡፡ ‹የፍቅር ባትሪያችንን› ሁልጊዜ ሙሉ ማድረግ አለብን፤ ካለበለዚያ እምነታችን አይሰራም፡፡ እንደክርስቲያን በፍቅር መመላለስን ለእምነታችንና ከእግዚአብሔር ጋር ላለን ግንኙነት እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ቆጥረን ለማግኘት የማንተጋ ከሆነ ችግር ውስጥ እንገባለን፡፡

የፍቅርን ህይወት እንፈልገው ከዚያም እምነታችን ሲጠነክርና ሲያድግ ትመለከታላችሁ፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር ቅድሚያ ሲመጣ፣ ሌላው ሁሉ ይከተላል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! እምነቴ ያለፍቅር ዋጋ-የለሽ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ እባክህን በፍቅርህ የተጥለቀለቀ ህይወት እንድኖር እርዳኝ፡፡ ፍቅርህን አንድቀበልና የሰጠኸኝን ፍቅር ለሌሎች ማካፈል እንድችል ምራኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon