የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ሥጦታዎች

የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ሥጦታዎች

ስለመንፈሳዊ ነገርም ወንድሞች ሆይ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ አሕዛብ ሳላችሁ በማናቸውም ጊዜ እንደምትመሩ ድምፅ ወደሌላቸው ወደ ጣኦታት እንደተወሰዳችሁ ታውቃላችሁ፡፡ (1 ቆሮ 12÷1 ተመልከት)

በክርስትና ታሪክ ውስጥ ስለመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ሥጦታ ብዙ ተጽፈዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ሥጦታ አስፈላጊነትና የእኛንም ችላ አለማለት አስፈላጊነትን ያስተምረናል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ብዙ መረጃዎች የሚገኙ ቢሆንም እንኳ ብዙ ሰዎች በሙሉ ስለዚህ ስጦታ አያውቁም፡፡ እኔ እራሴ አንድም ቀን ቤተክርስቲያንን ለረጅም አመታት ስከታተል አንድም ጊዜ ስለዚህ የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ሥጦታ ትምህርት ሰምቼ አላውቅም ምን እንደሆኑ እንኳ አላውቅም ነበር፡፡ ሌላው ይቅርና ለእራሴ የነበረኝን አላውቅም ነበር፡፡ ብዙ የተለያዩ

‹‹ተሰጥኦ›› ወይም በአዲሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ‹‹ሥጦታዎች›› እንደሚለውና በሌላ አገላለፅ በልዩ መልዕክተኛ የሚሰጥ ኃይል ለተወሰኑ ክርስቲያኖች በልዩ ሁኔታ የሚሰጥ ነው፡፡ (1 ቆሮ 12÷8-10 ተመልከት) ሥጦታዎች የተለያዩ ናቸው ነገር ግን ከአንዱ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ በዚህ ፀጋ ለመፀቀም እግዚአብሔር እንዲመራን ስንፈቅድ እነዚህ ፀጋዎች በሕይወታችን በተለያዩ አቅጣጫዎች ኃይልን ይጨምሩልናል፡፡ (1 ቆሮ 12÷8-10 ተመልከት) የፀጋ ሥጦታዎችን እንዲህ ይዘረዝራል፡፡ የእውቀት ቃል፣ እምነት፣ መናፍስት የመለየት የፈውስ ፀጋ የድንቅና የተዓምራት፣ የትንቢት፣ መንፈስን የመመርመር ፀጋ፣ በተለያየ ልሳን የመናገር ፀጋ፣ ልሳንን የመተርጎም ፀጋዎች ናቸው፡፡

እነዚህ ሁሉ ችሎታዎች፣ ተሰጥኦዎች፣ ፀጐችና ድሎች የልዕለ ተፈጥሮ ኃይላት አማኞች ከአቅማቸውና ከመደበኛው አካሄድ በላይ በሆነ መንገድ ነገሮችን የሚያደርጉበትና የሚፈጽሙበት ለአማኞች ሁሉ የተሰጠ ነው፡፡ ማንኛውንም መንፈሳዊ ፀጋ ሥጦታ በራሳችን ጊዜ እንድንሰራ ልናስገድደው አንችልም፡፡ እነዚህን ፀጋ ሥጦታዎች ሁሉ በብርቱ መፈለግ አለብን፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ራሱ መቼና በማን በኩል እንደሚሠራ ይመርጣል፡፡ ስለመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ሥጦታዎች በተመለከተ እግዚአብሔርን በመጠየቅ ተጠባበቀው፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- በድካም ልትኖር አይገባህም፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ኃይል ዛሬና ሁሌም አለልህና ነው፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon