ጠባቡ መንገድ መልካም ስፍራ ነው

ጠባቡ መንገድ መልካም ስፍራ ነው

በሩ ጠባብ ነው (በግፊት የሚያዝ) ደግሞም ወደ ሕይወት የሚወስደው መንገድ የጠበበ እና የተጨናነቀ ነው፤ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው። (ማቴዎስ 7:14)

ምናልባት ከጥቂት ዓመታት በፊት ያደረግከውን ነገር አሁን ለማድረግ ብትሞክር ህሊናህን የሚረብሽ ነገር ሊሆን ይችላል። ከአምስት ዓመት በፊት ምንም ሳይረብሽህ ቀርቶ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አሁን ስህተት መሆኑን ስለገለጠልህ ደግመህ ለማድረግ አታስበውም።

እግዚአብሔር ስለነገሮች ይናገረናል፤ ለማረም አብሮን ይሠራል፤ ከዚያ ለጥቂት ጊዜ እንድናርፍ ያደርገናል። ግን በመጨረሻ፤ አሁንም እስካደመጥነው ድረስ፤ እሱ ሁልጊዜ ስለ አዲስ ነገር ያወራናል።

እንደ እኔ ከነበርክ በአንድ ወቅት በሰፊ እና በግዴለሽነት ጎዳና ላይ በህይወት ውስጥ ተመላልሰሃል፤ አሁን ግን በጠባብ መንገድ ላይ ነህ። አንድ ጊዜ እግዚአብሔርን “መንገዴ እየጠበበ እና እየጠበበ ያለ ይመስላል” ማለቴን አስታውሳለሁ። እግዚአብሔር የሚመራኝ ጎዳና በጣም እየጠበበ ከመሄዱ የተነሳ ለእኔ ምንም ቦታ እስከማይኖረኝ ደርሷል የሚል ስሜት እንደነበረኝ አስታውሳለሁ። ጳውሎስ “ከእንግዲህ እኔ የምኖር አይደለሁም ግን በእኔ የሚኖረው ክርስቶስ ነው” ማለቱ ምንም አያስደንቅም (ገላትያ 2፥20 ን ተመልከት)። ኢየሱስ በእኛ ውስጥ ለመኖር ሲመጣ እርሱ ቋሚ የሆነ ስፍራ በመያዝ ለአሮጌው የራስ ወዳድነት ባህርያችን ስፍራ እየጠበበው እስከሚሔድ ድረስ በቀስታ በሕይወታችን ውስጥ የእርሱን መገኘት እያሰፋው ይሔዳል።

በጠባብ መንገድ ላይ እንዳለህከተሰማህ – ቀድሞ ታደርገው የነበረውንማድረግ እንደማትችል ወይም በአንተ ላይ ያሉ ክልከላዎችበጣም ጥብቅ እንደሆኑ ከተሰማህ- ከዚያ ተበረታታ። የእግዚአብሔር መገኘትበእናንተ ውስጥ እንዲኖር የድሮውራስ ወዳዱ ማንነትህእያነሰ ነው።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ ለእግዚአብሔር የበለጠ ስፍራ እንደሚሰጡ በማወቅ ክልከላዎችህን ተቀበል።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon