ፈተናዎች ማለፍ

ፈተናዎች ማለፍ

ልብንና ኩላሊትን የምትመረምር ጻዲቅ አምላክ ሆይ፤የክፉዎችን አመጽ አጥፋ፤ጻድቁን ግን አጽና፡፡ – መዝ 7፡9

ህይወት ቁርጠኝነታችንንና በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት በሚፈትኑ መከራዎች የተሞላች ነች፡፡ያጋጠመን የከፉ አስጊ ማስስፈራሪያም ሆነ የየዕለቱ አስቸጋሪ ነገሮች የባህሪያችን ጥራት በቋሚነት መፈተኑ አይቀርም፡፡

እግዚአብሔር ልባችንን፣ስሜቶቻችንንና አዕምሯችንን እንደሚፈትን መዘንጋት ትልቅ ስህተት ይሆናል፡፡አንድን ነገር መፈተን ማለት ምን ማለት ነው? አደርጋለሁ ያለውን ያደርግ እንደሆነ ጫና በመጨመር ማየት ነው፡፡በጫና ውስጥ ጸንቶ ማለፍ ይችላል? ሰሪው ይችላል ብሎ በሚያምነው መጠን መስራት ይችላል?በእውነተኛ መለኪያ እና ጥራት ሲለካ እውነተኛ ሆኖ ይገኛል?

እግዚአብሔርም እኛን እንዲሁ ነው የሚያደርገን፡፡

ዛሬ እየተፈተናችሁ ነው? ቁልፉ ባይገባችሁ እንኳ እግዚአብሔርን አምኖ መቀጠል ነው፡፡እውነቴን ነው አንዳንዴ በእግዚአብሔር መታመን ማለት ያልተመለሱ ጥያቄዎች ይኖራሉ ማለት ነው ነገር ግን ጥርጣሬያችሁን ትታችሁ ስትቀጥሉ ገንብቶ ጠንካራ ያደርጋችኋል ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ ስፈተን ዝግጁ፣በጫና ማለፍ የምችል ምንም መጣ ምን አንተን የምከተል መሆን እፈልጋለሁ፡፡በእያንዳንዱ ቀን፣ባልተመለሱ ጥያቄዎቼ በምቸገርበት ጊዜም ቢሆን እንዴት በአንተ መታመን እንዳለብኝ አሳየኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon