አቤቱ ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትቅረብ& እንደ ቃልህም አስተዋይ አድርገኝ፡፡ መዝ 119 169
የትኛውንም ዓይነት ፀሎት ስንፀልይ የጥሞና ፀሎት ወይም የቃልኪዳን ፀሎት ለዓላማ ስኬት፣ የምልጃ ፀሎት ወይም የመግባባት ፀሎት (የክዳን) የምሥጋና ፀሎት የአምልኮ ፀሎት የእግዚአብሔር ቃል ወሳኝ ማጣፈጫ ወይም ቅመም ነው፡፡ ሁልጊዜ ፀሎቶቻችን ውጤታማ የሚሆኑት የእግዚአብሔርን ቃል በማስታወስና መሠረት በማድረግ በእምነት ስንፀልይ እግዚአብሔር እንደተናገረው እንደቃሉ መልስ ይሰጣል፡፡ እንዲሁም ደግሞ ፀሎታችን ይበልጡኑ ውጤታማ ይሆናል ብዬ የማምነው በመንፈስ ቅዱስ ስመራ ነው፡፡
በመንፈሣዊ ሕይወታችን ጠንካራና ሚዛናዊ ለመሆን ሁለቱም የእግዚአብሔር ቃልና የመንፈስ ቅዱስ ምሪት በፀሎታችን ውስጥ በጣም ያስፈልጋል፡፡ ሰዎች ከመጠን ያለፈ መለኮታዊ ልምምድ ሲፈልጉ ወይም ከመጠን በላይ በመንፈሳዊ ጉዳይ ላይ ሲጠመዱ በመታለል በጣም ስሜታዊያን በመሆን በሃሣብ የመከፋፈል አደጋ ያጋጥማቸዋል፡፡ በዚያው ልክ በቃል ብቻ ላይ የታሰርን ያደርጋል፡፡ የእግዚአብሔር ቃልና የእግዚአብሔር መንፈስ በአንድት ስንይዝና ጽኑና ሚዛናዊ መሠረት ያለው በእውነት ላይ የተመሠረተ በፀጋና በሃሴት የተሞላ ኃይለኛ ሕይወት እንኖራለን፡፡ እኛን የሚያስፈልገው መሠረት ያለው የፀና የእግዚአብሔር ቃልና የመንፈስ ቅዱስ ፈቃድና ስሜት መከተል ነው፡፡
ከእግዚአብሔር ቃል ጋርና እንደመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ መፀለይ እንደእግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ የፀሎት ሕይወት ውስጥ እንድንኖር ይረዳናል፡፡ እንዲሁም የፀሎታችን ውጤታማና እጅግ ፍሬያማ ሕይወት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ ማንኛውም ነገር ብታደርግ ፀሎትህ በእግዚአብሔር ቃል የተሞላና በመንፈስ ምርት የተጎዳ እንዲሆን አበረታታሃለሁ፡፡ በሕይወትህ እጅግ ብዙ ውጤት ታያለህ፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- የእግዚአብሔር ቃል የመንፈስ ሰይፍ ነው፡፡ እርሱም ሰይጣንን የምትዋጋበት የጦር መሣሪያ ነው፡፡