በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ ከመደሰት እና መልካም ከማድረግ የተሻለ ለእነሱ ምንም የተሻለ ነገር እንደሌለ አውቃለሁ ፡፡ – መክብብ 3፡12
በህይወቴ ከተማርኳቸው ትልልቅ ነገሮች አንዱ ማንም ሰው ደስተኛ ሊያደርገኝ እንደማይችል ነው፡፡ ለራሳችን ደስታን እንድንሰጥ እግዚያብሔር አስፈላጊውን ሃላፊነት ሰጥቶናል፡፡ በጣም በርካታ ሰዎች ሌሎች ሰዎች ጠባያቸውን ካላስተካከሉ፤ አሊያም ነገሮች እንደፈለጓቸው ካልሆኑ ደስ አይላቸውም። ሁል ጊዜ ደስታችንን በተለያዬ ሰዎችና ጉዳዮች ላይ እንዲወሰኑ እናደርጋለን ይሁንና እግዚያብሔር ግን ደስታችንን ከእርሱ ዘንድ እንድናገኝ ፍላጎቱ ነው፡፡
ኮንፍራንስ ባደረግንበት ማግስት ባለቤቴ ዳዊት ወደ ጎልፍ መጫዎቻ ቦታዎች በሚሄድበት ጊዜ እጅግ በጣም እከፋ ነበር ምክንያቱም ወደ ገበያ ቦታዎች አብሮኝ እንዲሄድና ከእኔ ጋር ፊልም እንዲይ ስለምፈልግ፡፡ ነገር ግን እግዚያብሔር ሁለታችንም የምንዝናናበት መንገዶች የተለያዩ መሆኑን አሳየኝ፡፡
ይህ አንዱ ምሳሌ ብቻ ሲሆን ልክ እንደዚህ በጣም በርካታ ነገሮች ከሌሎች ሰዎች በመጠበቅ እራሳችንን ለማስደሰት እንሞክራለን፡፡ እግዚያብሔር እርሱን እንድንመለከትና በእርሱ ላይ እንድንደገፍ ነው የሚፈልገው፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
እግዚያሔር ሆይ ደስታዬ በሌሎች ነገሮች ላይ የሚመሰረት ሳይሆን በአንተ ላይ የሚመሰረትና የሚደገፍ ነው፤ በአንተ ላይ እንድደገፍና ከአንተ ብቻ እንድጠብቅ እርዳኝ፡፡