መልካም የሆነ አመለካከት ዉጤታማ ያደርጋል

መልካም የሆነ አመለካከት ዉጤታማ ያደርጋል

እግዚአብሔርሆይ፤ጸሎቴንስማልኝ፤የአፌንምቃልአድምጥ።(መዝ 54:2 )

ሁላችንም ጸሎታችን ዉጤት እንዲኖረዉና ከሱጋር በሚኖረን ንግግርም እሱ በእኛ እና በሌሎች ህይወት ዉስጥ ፍቀዱ በሚገባ እንዲፈጸም እና ዉጤታማ አንዲሆን እንፈልጋለን፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ ሲናገርም፣ “ስለዚህኀጢአታችሁንእርስበርሳችሁተናዘዙ፤ትፈወሱምዘንድአንዱለሌላውይጸልይ።የጻድቅሰ ውጸሎትኀይልአለው፤ታላቅነገርምያደርጋል” (ያዕቆብ 5:16) ፡፡ ዉጤት ያለዉ ጸሎትና ብዙ ለመቀበል ከፈለግን፣ ዉጤታማ እንዳይሆን የሚያደርጉትን ደግሞ ማወቅ አለብን፡፡ ሁሉም ጸሎቶቻችን ዉጤታማ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፣ አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ፍቃድ የሌለበትን ነገር ለማግኘት አጥብቀን እንጸልያለን፤ እንዲህ አይነቱ ጸሎት ዉጤት የለዉም፡፡አንዳንድ ጊዜ የምንጸልየዉ ተበሳጭተን ወይም ተጎድተን ባለንበት ስሜት ዉስጥ ሆነን ይሆናል፤ እንዲህ አይነቱ ጸሎትም ዉጤት አይኖረዉም፡፡

እግዚአብሔር በቃሉ፣ ዉጤት ያለዉ ጸሎት ለመጸለይ ምን ማድረግ እንዳለብን ይነግረናል፡፡ ዉጤታማ የሆነ ጸሎት ህግንና መርሆዎችን በመጠበቅ የምናደርገዉ አይደለም፡፡ዉጤታማ ጸሎት በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሰረተ፤ ቀላል የሆነ፣ በቅንነት፣ በእምነት የተሞላ፤ ከህግና መመሪያ ጋር ያልተገናኘ፣ ይልቅከልብና መልካም ከመሆን ጋር የተያያዘ ነዉ፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡ ጥሩ ያልሆነ አመለካከት የሚቀየረዉ ራሳችን ለመቀየር በምናደርገዉ ዉሳኔ ነዉ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon