ሰዎች ያለገደብ ተፈላጊ እንደሆኑ አሳውቅ

ሰዎች ያለገደብ ተፈላጊ እንደሆኑ አሳውቅ

አባቴና እናቴ ቢተዉኝም እንኳ ጌታ እንደ ልጁ አድርጎ ይቀበለኛል ፡፡ – መዝሙር 27፡10

በዕለት ተዕለት ሕይወት የምናገኛቸው በርከት ያሉ ሰዎች እግዚአብሔር ከገደብ ያለፈ እንደ ልጆቹ ለኛ ዋጋ እንዳለው እንደማይረዱ ተረድቻለሁ፡፡ እንደማይረቡ እና ዋጋ የሌላቸው አድርገው ክፉ እንደያስቡ ዲያቢሎስ በደንብ እየሰራ እንደሆነ አስባለሁ ነገር ግን ይህን ውሸት እና ክስ ሰዎቹን በመገንባት ፣ በማበረታታት እና በማነጽ እንደምናከሽፈው አውቃለሁ፡፡

ይህን የምናደርግበት አንድኛው መንገድ በማሞካሸት ነው ፤ ይህ ስጦታ ደግሞ በአለም ውስጥ አለ የሚባል ነገር ነው፡፡ በትንሹ ሰዎችን ማሞካሸት ቀላል ነገር ይመስለናልን ይህን ማድረግ ግን በራስ መተማመን የሌላቸው እና ጥቅም የለኝም ብለው ለሚያስቡ ሰዎች ከፍተኛ ብርታትን ይሰጣቸዋል፡፡

ግብን በማስቀመጥ አምናለሁ ፤ ሰዎች በማበረታት አቅጣጫ መልካም ልማዶችን ለማዳበር ከእግዚብሔር ጋር ስሰራ ራሴን በትንሹ ሶስት ሰዎችን ማሞካሸት እንዳለብኝ አድርጌ ለራሴ ስራ እሰጣለሁ፡፡ እናንተም እንዲሁ እንድታደረጉ እና በጣም ሰዎችን የምታበረታቱ እንድትሆኑ እመክራችኋለሁ፡፡

መጽሀፍ ቅዱስ የተጣልክ እንኳን ብሆንም እግዚአብሔርም ግን እንደ ልጁ አድርጎ ይቀበላል ይላል፡፡ የተረሱ የሚመስላቸውን ሰዎች ፈልገን የሚረቡ ያላቸው ሰዎች እንዲሆኑ እንገባቸው ፤ እግዚአብሔር እንደሚወዳቸው ይወቁ፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ እግዚአብሔር እንደ ራሱ ልጆች አድርጎ እንደሚወዳቸው የማያውቁ ሰዎችን አሳየኝ ፡፡ እንዳበረታታቸው እና ረብ ያላቸው መሆናውን እንድነግራቸው፡፡ በመንገዳቸውም ውሰደኝ

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon