በመንፈስ ተመራ

በመንፈስ ተመራ

በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ፡፡ ገላ 5÷ 25

የዛሬው ጥቅስ የምንናገረው በመንፈስ ስለመኖርና በመንፈስ ስለመመላለስ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በመንፈስ መመራት ከምለው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ብዙ ነገሮች ሊመሩን ይፈልጋሉ፡፡ ሰይጣን፣ ሥጋ (የእኛ ሰውነት ሃሠብ፣ ፈቃዶቻችን፣ ወይም ስሜቶቻችን)፣ ወይ መንፈስ ቅዱስ፡፡ ድምፃቸውን የሚያሰሙንና የሚናገሩን ብዙ ነገሮች በዓለም አሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ አብዛኛዎቹ በአንድ ጊዜ ያንን ያደርጋሉ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ እንዴት እንደምንመራ መማራችን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ አስታውስ፡- እሱ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያውቅና በእኛ ውስጥ ኖሮ ሊያግዘን የተላከልን በመሆኑ እግዚአብሔር ለሕይወታችን ያቀደውን እንዲፈፀምና እርሱ የፈቀደው ሁሉ ለእኛ እንዲሆን ነው፡፡

መንፈስ ቅዱስ በእኛ የሚኖረው እኛን ለመረዳት ነው፡፡ የእርሱ እርዳታ ምናልባት በመጀመሪያ ደስ ላያሰኝ ይችላል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ይመስገን እርሱ የሚቀጥልና በእኛ ተስፋ የማይቆርጥና የማያቋርጥ ነው፡፡ በየቀኑ ሕይወታችን ቀና አድርገን በሙሉ ኃይላችን መንፈስ ቅዱስ ሆይ በእያንዳንዱ የሕይወቴ ጉዳይ ላይ እጋብዝሃለው! እንበል፡፡ መንፈስ ቅዱስን በእያንዳንዱ የሕይወታችን ጉዳይ ላይ ስንጋብዝ እርሱ ይመጣል፡፡ ይናገርሃል፣ ይመራሃል፣ ያስተካክልሃል፣ ይረዳሃል፣ ኃይል ይሰጥሃል እንዲሁም ይመራሃል፡፡ ሌሎች ኃይላት ምናልባት ሊመሩህ ይሞክሩ ይሆናል፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ እንድትቋቋማቸው ኃይል ይሰጥሃል እርሱንም እንድትከተል ያስችልሃል፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- ሕይወትህን ማን እየመራ እንዳለ እራስህን ጠይቅ፡፡ አንተነህ፣ ሌሎች ሰዎች፣ ስሜትህ፣ የሰይጣን ውሸቶች ወይስ መንፈስ ቅዱስ;

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon