ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ፡፡ 1 ተሰ 5÷21
ከእግዚአብሔር ግልፅ የሆነና ከተጭበረበረ ድምፅ የፀዳ ድምፅ ለመስማት የሚመጣው ጊዜ በጌታ ፊት በተከታታይነት በጌታ ፊት በማሳለፍ፣ ቃሉን በመማር፣ የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ሳይኖረን የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማት ስህተት ነው፡፡ የተፃፈውን የተገለጠ የእግዚብሔር ቃል ማወቅ ከመጭበርበር ይጠብቃል፡፡
የእግዚአብሔርን ቃል እውቀት ሳይኖረን ከእግዚአብሔር ለመስማት መሞከር ግድ የለሽነትና አደገኛም ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ የሚፈልጉ ሰዎች ነገር ግን ቃሉን ለማንበብና ለፀሎት እራሳቸውን ለስህተት እራሳቸውን ያጋልጣሉ፡፡ ምክንያቱም ክፉ መንፈስ እንደዚህ ለመስማት የምፈጥን ባላቸው ጆሮዎች ሹክ ለማለት ጉጉት ለራሳቸው ነው፡፡ ሰይጣን ኢየሱን ለመፈተን የተለያዩ ነገሮችን ሳያመጣበት ይመክት የነበረው እንዲህ ተብሎ ተጽፈዋል ብሎ ቃሉን በመጥቀስ አባባሉ ትክክል እንዳልሆነ ያስረዳና ስህተት መሆኑን ለጠላት ውሸት መልስ ይሰጥ ነበር (ሉቃ 4 ተመልከት)፡፡
ማንኛውንም ሃሳብን ማመዛዘን ማስረዳት፣ ከእግዚአብሔር ቃል ተያይዞ የሚመጣውን ትምህርት በቃሉ መመዘን አለበት፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል የማናውቅ ከሆነ ምንም የጽንሰ ሃሳብ ምርመራ አመለካከቶችና ሃሳቦች ውስጥ እራሳችን ማስገባት የለብንም፡፡ ጠላት ጭፍን ግምት በእኛ ስሜትን የሚነካ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ሃሣቦች ትክክልና እውነት አላቸው ማለት ከእግዚአብሔር ነው ማለት አይቻልም፡፡ የምንሰማው ደስ ሊለን ይችላል፡፡ ነገር ግን ነገሩ ለእኛ መልካም ሆነ ማለት ነገሩ ከእግዚአብሔር ነው ማለት አይደለም፡፡ ምናልባት ለስሜታችን መልካም የሆነ ነገር ይሰማል ማለት እንደእግዚአብሔር ያለ ሠላም አይሰጠንም፡፡ የእግዚአብሔር ምክር ሁልጊዜ ሰላምንና የሕሊና ዳኝነት ለሕይወታችን ይሰጣል፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ ዛሬ፡- ሁሉም ነገር ፊትን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር አድርግ ምክንያቱም ቃሉ ለእውነት ቃል መመዘኛ ስለሆነ ነው፡፡