በእግዚአብሔር እንድንደሰት ነዉ የተጠራነዉ

ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን። – 1 ቆሮ 8:6

ኛ ከእግዚአብሔር ምቾት ልንቀበል ያስፈልገናል፡፡ አክብሮት አልባ እንሁን እያልሁ አይደለም ግን ደግሞ እርሱን መፍራት የለብንም፡፡ የሁሉም አማኝ የመጨረሻዉ ጥሪ በእግዚአብሔር መደሰት እንደሆነ አምናለሁ፡፡ በአባታችን እንድንደሰት ተጠርተናል ምክንያቱም አባታችን ህይወት ነዉና ደግሞም በእግዚአብሄር ከልተደሰትን ህይወትን ደስተኛ ማድረግ አንችልም፡፡

አንዳንድ ጊዜ እርሱን ለማገልገል ራሳችንን ስናወጣጥር፣ ጸጋችንን ስንፈልግና ጊዜአችንን በአገልግሎት ሩጫ ስንጨርስ በእርሱ መገኘት መደሰት አንችልም፡፡ ይህ በእኔ ተከስቶ ያዉቃል፡፡ በአገልግሎቴ ለአምስት አመታት እግዚአብሔር ፍሬን እንድይዝ ማደረግ ነበረበት ምክንያቱም እኔ ለእርሱ በማደርግለት ነገር ኮርቼ በእርሱ መደሰትን ረስቼ ነበረና፡፡

በምናደርጋቸዉ ነገሮች ምክንያት በራሳችን እንዳንኮራ ልንጠነቀቅ ያስፈልጋል፤ ምክንያቱም እርሱ እግዚአብሔር የሚፈልገዉ ነገር አይደለም፡፡ እንደ አባታችን እርሱን እንድናዉቀዉና በእርሱ እንድንደሰት ነዉ የሚፈልገዉ፡፡

ስለዚህ ልጠይቃችሁ፡ በስራችሁ ምክንያት እየተኩራራችሁ ነዉ? ወይስ በእዉነት በእግዚአብሔር እየተደሰታችሁ ነዉ? 

የጸሎት መጀመሪያ

አባት እግዚአብሔር ሆይ! በአንተ መደሰት እፈልጋለሁ፡፡ ከአንተ ጋር መሆንና ህብረት መፍጠር እጅግ ጥሩ ነገር ነዉ፡፡ የህይወቴን ዓላማና ደስታ በአንተ ብቻ ነዉና ማገኘዉ ትዕብቴን ወዲያ ጥዬ ራሴን በፊትህ ትሁት አደርጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon