በእግዚእብሔር ኃይል መታመን

እምነታችሁምበእግዚአብሔርኃይልእንጂበሰውጥበብእንዳይሆን፥ቃሌምስብከቴምመንፈስንናኃ
ይልንበመግለጥነበረእንጂ፥በሚያባብልበጥበብቃልአልነበረም።(1ኛ ቆሮንቶስ 2:4–5)

ትምህርት ወሳኝ ነገር ቢሆንም የእግዚአብሔር ጥበብ ከምድራዊዉ እዉቀትና ፍልስፍና እንደሚበልጥና ዋጋ ያለዉ መሆኑን መቼም መርሳት የለብንም፡፡ ሐዋርያዉ ጳዉሎስ በዘመኑ በጣም የተማረ ሰዉ ነበር፣ ነገር ግን ስብከቶቹ ኃይል ያላቸዉ እሱ ካለዉ እዉቀት የተነሳ ሳይሆን ከእግዚአብሔር መንፈስ የተነሳ መሆኑን አስረግጦ ይነግረናል፡፡

ብዙ ሰዎች ከዩንቨርሰቲ በከፍተኛ ማዕረግና በብዙ ዲግሪዎች ተመርቀዉ ስራ ለማግኘት እንደሚቸገሩ አዉቃለሁ፡፡ ኮሌጅ ለመግባት እድሉን ያላገኙ በእግዚአብሔር በመደገፍ እሱ በሰጣቸዉ ሞገስ ስራቸዉን በስኬት የፈጸሙም እንዳሉ አዉቃለሁ፡፡ መታመናችሁ ማን ላይ ነዉ?በእግዚአብሔር ነዉ ወይስ በእዉቀታችሁ? ምንም ሆነን ብንገኝ፣ የትኛዉም እዉቀት ቢኖረንም፣ መታመናችን በክርስቶስና በእሱ ኃይል ላይ ብቻ መሆን አለበት፡፡

ጳዉሎስ 1ኛ ቆሮንቶስ 1:21 ላይ በእግዚአብሔርጥበብምክንያትዓለምእግዚአብሔርንበጥበቧስላላወቀችዉ፥በስብከትሞኝነትየሚያምኑ ትንሊያድንየእግዚአብሔርበጎፈቃድእንደ ሆነ ተናግሯል። የሚያሳዝነዉ ግን፣ አብዛኛዉን ጊዜ ሰዎችበጣም የተማሩሲሆኑ፣ ዝቅ ለማለትና በእምነታቸዉ እንደልጆች ለመሆን ሲቸገሩ እናያለን፡፡ ጥንቃቄ የማናደርግ ከሆነ የበዛ የዓይምሮ እዉቀትና ምክንያታዊነት ችግር ሊፈጥርብን ይችላል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔርን ማወቅ የምንችለዉበዓይምሯችን ሳይሆን በመንፈስና በልባችን ነዉ፡፡ በህይወት ሁሉ እምነትህ በሰዉ ፍልስፍና ላይ ሳይሆን
በእግዚአብሔር ኃይል ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ማድረግ አለብህ፡፡”


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡ በህይወትህ ሁሉ የሚያጋጥሙህን የትኛዉንም እንቅፋት የእግዚአብሔር ኃይል ያሸንፍልሃል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon