እግዚአብሔርን እንዴት ነገር ለመንኩት እርሷንም እሻለሁ፣ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ፡፡ መዝ 27፡4
ከእግዚአብሔር የመስማት ፍላጎት ካለን የእርሱን መሻት የሕይወታችን ቀዳሚ መሆን አለበት፡፡ ዳዊት ከዛሬው የዕለት ጥቅሳችን እንደምንረዳው የሕይወቱ ማጠቃለያና አስፈላጊ ጉዳይ ያደረገው በዘመኑ ሁሉ በእግዚአብሔር ማግኘት ውስጥ መኖር ነው፡፡
ዳዊት በእግዚአብሔር አብሮነት ውስጥ ሆኖ ብዙ አጋጣሚዎችን፣ ድሎችንና መደላደሎችን ለመቀዳጀት ችለዋል፡፡ ከእግዚአብሔር አብሮነት የተነሣ በጣም የሚያስፈራውን ሃያሉን ጎልያድ ከአምስቱ ጠጠሮች ውስጥ በመጀመሪያ በወነጨፈው የድንጋይ ጠጠር ነው፡፡ እግዚአብሔር ተራ የበግ እረኛ የሆነውን የመረጠው ገና ከቤተሰቡና ከወንድሞቹ መካከል የሁሉ ታናሽ ሆኖ ሳለ ነው፡፡
ዳዊት ከተለያዩ ድሎችና ልምምዶች እንዲሁም የእግዚአብሔርን አብሮነት ካየ በኋላ እንኳ ጥማቱ እግዚአብሔር ነበር፡፡ ይህ የሚያረጋግጥልን የቱንም ያህል ብዙ የተለያዩ ድሎችን በሕይወታችን ብንለማመድም እንኳ እግዚአብሔን እራሱ መፈለግ እንዳለብን፡፡ ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ የዳዊት ትኩረት እግዚአብሔርን በጥልቀት መፈለግ ላይ ነበር፡፡
ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ምርት ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን ድምፁን ለመስማት ሌሎችን ነገሮች ከጎን ለመጣል አይፈልጉም፡፡ ዳዊት ግን ሁሉን ነገር ወደ ጎን በማድረግ በዘመኑ ሁሉ አንድ ነገር ላይ እርሱም እግዚአብሔርን የሕይወቱ ዘመን ምርጫ አደረገ፡፡
ከትላንት ይልቅ ዛሬ ሕይወታችን ሊያረካ የሚለው ከውስጣችን እግዚአብሔርን በጥልቀት መፈለጋችን እንደሆነ አምናለሁ፡፡
የዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ላንተ፡- በሕይወትህ ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን ፈልግ፡- ዛሬና ሁልጊዜ.