እግዚአብሔር ለፃድቅ ሰው ፀሎት መልስ ይሰጣል

እግዚአብሔር ለፃድቅ ሰው ፀሎት መልስ ይሰጣል

የፃድቅ ሰው ፀሎት በሥራም እጅግ ኃይል ታደርጋለች፡፡ ያዕ 5÷16

ሰዎች በፀሎት ሕይወታቸው የሚታገሉት አብዛኛውን ጊዜ እነርሱ ቅዱሳንና ፃድቃን እንደሆኑ ስለምሰማቸውና ባሕሪያቸውን በማረም ሙከራ ሲያደርጉ የፀሎታቸው መልስ እንደሚያገኙ ተስፋ በማድረግ ነው፡፡ እውነታው ግን እኛ ዳግመኛ ስንወልድ ወዲያው ፀድቀናል፡፡ እኛ ምንም ዓይነት መልካምና ትክክለኛ ነገር ያደረግነው የለም፡፡ ነገር ግን መቶ ፐርሰንት (100%) በክርስቶስ ፃድቃን ነን፡፡ 2ኛ ቆሮ 5÷21 ይህንን ይነግረናል፡፡ እርሱ ኃጥያት የማያውቀውን ስለ እኛ ኃጢያት አደረገው፡፡ እኛ በእርሱ የእግዚአብሔርን ጻድቅ በእርሱ እንድንሆን አደረገ፡፡ በጻድቅ እና በመልካም (ትክክል) ባሕሪ መካከል ልዩነት አለ፡፡ ጻድቅ መሠረታችንን የሚገልፅ የእኛን ቦታ ወይም ሁኔታ በእግዚአብሔር ፊት ከኢየሱስ ደም የተነሣ ያለንን ያመለክታል፡፡ እኛ እራሳችንን ፃድቅ ማድረግ አንችልም፡፡ ነገር ግን የኢየሱስ ደም ብቻ በእግዚአብሔር ፊት ፃድቅ ያደርገናል፡፡ ምንም ከዚህ በፊት ኃጢያት እንዳላደረግን አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርበናል፡፡ እግዚአብሔር እኛን የሚያየን እንደ ፃድቅ ነው፡፡

ምንም እንኳ እኛ ስህተት የምንሰራ ብንሆንም እሱ የሚያየን እንደ ጻድቃን ከእግዚአብሔር የተሰጠን መብት የመፀለይ እና እግዚአብሔር እንደሚሰማንና መልስ እንደሚሰጠን መብት ሰጠን፡፡ ሁልጊዜ መልካም ነገር አድርግና የቻልነውን ያህል ባሕሪህን በመልካም ሥነምግባር አንጽ፡፡

ይህም ለእግዚአብሔር ያለህን ፍቅርህን ግለጽበት፡፡ ነገር ግን ማስታወስ ያለብህ ፀሎትህን የምሰማውና የምመልሰው እርሱ መልካም ስለሆነ እንጂ ከአንተ የተነሣ እንዳይደለ ነው፡፡

ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- በእግዚአብሔር ፀጋ ጻድቅ ተደርገሃል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon