ውስጣዊ ህይወት

‹‹¸… ፊተኛይቱም ድንኳን በዚህ ገና ቆማ ሳለች፥ ወደ ቅድስት የሚወስደው መንገድ ገና እንዳልተገለጠ መንፈስ ቅዱስ ያሳያል›› (ዕብ.9፡8) ።

የብሉይ ኪዳን የማደሪያ ድንኳን ሶስት ክፍሎች አሉት፡፡ እነርሱም የደጅ አደባባይ፣ ሁለተኛው የቅድስት ተብሎ የሚጠራውና፣ ሶስተኛው ቅድስተ ቅዱሳን እርሱም ውስጠኛው መድረክ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ህልውና የሚገኘበት ቅድስተ ቅዱሳን በሚባለው ሥፍራ ሊቀ ካህኑ ብቻ ሊገባባት የሚችል ነው፡፡

እንደ የሰው ልጅነት እኛም ባለሶስትዮሽ ማንነት ያለን ሰዎች ነን፡፡ እኛ አካላችን የሆንን ሥጋ አለን፣ ነፍስ አለን፣ እንዲሁም መንፈስ አለን፡፡ ለዛሬ የመረጥነው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንዳስቀመጠው የውጪያዊ ማንነታችንን እውቅና እስከሰጠነው ድረስ እርሱም የስጋችንና የነፍሳችን ምሳሌ የሆነው ነው፤ ከዚያም ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚወስደው መንገድ የንፈሳችን ምሳሌ የሆነው አርሱ የተከፈተ አይደለም፡፡ በቀላል ቃላት ለሥጋችን ፍላጎትና የምንገዛ ከሆነ በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ መኖርና መደሰት አንችልም፡፡ ለምሳሌ የምቆጣ ከሆነ በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ መደሰት አልችልም፡፡

ሥጋዊ ክፍላችን ሁልጊዜ የራሱን ፍላጎቶች ያቀርባል፤ ምክንያቱም ሥጋችን ራስ ወዳድና የራሱን መንገድ የሚከተል ነው፤ ነገር ግን እነዚያን ፍላጎቶቹን ሁሉ አንሰጠው ወይም አናሟላለትም፡፡ በቀላሉ ግን እንዲህ ልንል እችላለን ‹‹ … ከዚህ በኋላ ምንም እውቅና አልሰጥህም፤ አንተ በእኔ ላይ ምንም ዓይነት ስልጣን የለህም፡፡›› ሥጋዊ ፍላጎቶቻችን ላለማሟላት የተቃውሞ አቋም ስንወስድ፤ እና እግዚአብሔርን እያከበርንና በህልውናው ውስጥ ለመኖር እንችላልን፡፡ ለዛሬው ያለው መልዕክታችን ቀላል ነው ‹‹ ለእኔነት አይሆንም፤ ለእግዚአብሔር ግን ይሆናል›› የሚል ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው እና ለኃጢአት የሞትን ነን፡፡ ኃጢአት አይሞትም፤ እርሱ ሁልጊዜ ወደ ራሱ ይስበናል፡፡ ነገር ግን እኛ ‹‹አይሆንም›› ማለት እንችላለን፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ የሚፈልገውን ሥጋዊ ፍላጎቱን በመመገብና ለሥጋዊ ባህርይው የልብ ትርታ ለሥጋዊ ምላሽ በመስጠት ለሥጋዊ ህይወት አትኑር፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon