ሰዎችም፣ ‘እዚህ ነው’ ወይም ‘እዚያ ነው’ ማለት አይችሉም፤ እነሆ፤ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና። – ሉቃ 17፡21
አንዳንድ ጊዜ ነገሮች እንዲቀየሩ እንጓጓለን ይሁንና ለውጡን ሊያመጣ የሚችለውን ነገር ለማድረግ ፈቃደኞች አይደለንም፡፡ በህይወቴ ውስጥ በሚያጋጥሙኝ ሁኔታዎች የተነሳ ሁልጊዜ እበሳጭ የነበረባቸው ገጠመኞች ብዙ ናቸው፡፡እግዚብሔር ችግሮቹን እንዲቀይራቸውና በአጠገቤም ያሉትን ሰዎች ሁሉ እንዲቀይራቸው እፈልግ ነበር ነገርግን ከሁሉ አስቀድሞ ውስጣዊ ማንነቴን እንዲቀይር በማሳየት ውጫዊ ማንነቴን እንደምቀይር አሳይቶኛል፡፡
ማቲ6፡33 እንዲህ ይላል:- ከሁሉ አስቀድማችሁ ግን የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን እሹ፤ እነዚህ ሁሉ ይጨመሩላችኋል። ስለዚህ የእግዚብሔር መንግስት ምንድነው? መፅሐፍ ቅዱስ ሲናገር የእግዚአያሔር መንግስት በአኛ ውስጥ ናት ይላል። ክርስቶስን ከተቀበላችሁ በእናንተ ውስጥ ይኖራል ማለት ነው፡፡ እናም በጣም ጤናማ ህይወት እንዲኖራችሁ ያደርጋል፡፡ ለዚህ ነው ውስጣዊ ህይወታችሁ ለእግዚያብሔር እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነው፡፡
በመጀመሪያ መንግስቱን እሹ መንፈስ ቅዱስ ወደውስጥ ማንነታችን እንዲገባ ማድረግ በውስጣችን እንዲሰራ መፍቀድ አለብን እሱም ህይወታችንን ይቀይረዋል፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
መንፈስ ቅዱስ ሆይ መንግስትህን በውስጤ እንዳዳብር በምትጠይቀኝ ወቅት ውጫዊ ማንነቴን መቀየር ላይ እንዳለፋ ጠብቀኝ ፣ በህይወቴ ውስጥ እንድትገባ እጋብዝሃለሁ፡፡