በፀሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ፀልዩ፡፡ ኤፌ 6÷16
በዚህ ለዛሬ ጥቅሶችን ጳውሎስ የሚለው በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስን ምርት በመከተል፣ የተለያዩ የፀሎት አይነት ዘዴዎች በመጠቀም በተለያዩ ሁኔታዎች መፀለይ አለብን ይላል፡፡ ነገር ግን እንዴት ነው ሁልጊዜ መፀለይ ያለብን; መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚመራን ነው; የምንፀልየው በአመስጋኝነት ሃሳብና ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር በመታመን፣ ልክ በዕለታዊ ሕይወታችን እንደምናደርገው ሃሣባችንን ወደ እርሱ በማድረግ በምናደርገውና በምንሰራው ሥራ መካከል የእርሱን ድምፅ መስማት ያስፈልጋል፡፡
በእርግጥ አምናለሁ እግዚአብሔር እኛ የፈለግነውን የፀሎት ሕይወት እንዲኖረንና ፀሎትን እንደድርጊት እንድናስበው እንደ አንድ የሕይወታችን ክፍል እንድንኖረው ነው፡፡ እንደ ውስጣዊ ማንነታችን የነገሮችን ሂደት እንደምያቀነባብር እንድናየው ነው፡፡ እርሱ የሚፈልገው እኛ በቀጣይነት እንድናወራውና እንዲነገረን እንዲሁም እንድንሰማው ነው፡፡ ይህም በመንገዳችን ሁሉ በፊቱ ሁልጊዜ በፊቱ እንድንፀልይ ወደ እርሱ ተጠግተን በጆሮአችን ወደ እርሱ ተጠግተን ድምፁን እንድንሰማው ነው፡፡ እኛ ብዙውን ጊዜ ስለሁኔታዎቻችን ፀሎት ለሚፈልጉ ጉዳዮቻችን በኋላ በፀሎቴ ሰዓት ስለዚያ ጉዳይ እፀልያለሁ እንላለን ወይም ደግሞ እንደምንፀልይ እናስባለን፡፡ ያኛው ሃሣብ ግን የጠላታችን የመስረቂያ ዘዴ ነው፡፡ ለምን በዛው ደቂቃ (ቅጽበት) የማትፀልየው; ለፀሎት ካለን የተሳሳተ የአእምሮ ቅንብር የተነሣ በትክክልና በጊዜ አንፀልይም፡፡ ነገሩ ቀላል የሚሆነው ልባችን ስናደምጥና ስናደርገው ነው፡፡ ነገር ግን ሰይጣን ነገሮችን ማወሳሰብና ፀሎትን ያደናቅፋል፡፡ እርሱ እኛ ዛሬ ነገ እያልን በተስፋ ስንጠባበቅ በጠቅላላ ጉዳዩን እንድንዘነጋ ይፈልጋል፡፡ የፀሎት ሃሣብ በውስጣችን በመጣ ጊዜ መፀለይ በጣም ቀላልና በቀጣይነት ለመፀለይና ተጣብቆ ከእግዚአብሔር ጋር በማንኛውም ሁኔታ ቀኑን ሁሉ የምንኖረው ነው፡፡
ዛሬ እግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ለእግዚአብሔር ማውራትን አታቁም፡፡