የመጀመሪያ ምላሽ (መፍትሔ)

የመጀመሪያ ምላሽ (መፍትሔ

አምላክ፣ አምላኬ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፣ ነፍሴ አንተን ተጠማች፣ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች እንጨትና ውሃ በሌለበት በምድረ በዳ፡፡ መዝ 63÷1

አንዳንድ ጊዜ ያለንበትን ሁኔታ ለእግዚአብሔር በፀሎት ከመንገራችንና የእርሱን ድምፅ ከመስማት በፊት ለራሳችን ለብዙ ጊዜ ስንጨነቅበትና ስንታገለው ሳስበው እገረማለሁ፡፡ ስለችግራችን ምክንያት እናበዛለን፣ እናመርራለን፣ እናጉረመርማለን፣ ለጓደኞቻችን እናወራለን፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር በጉዳዩ ላይ አንድ ነገር ቢያደርግ እንደምንፈልግ እናወራለን፡፡ ከሁኔታዎች ጋር በአእምሮአችንና በስሜታችን እንጨነቃለን፣ ቀላሉና ውጤታማ የሆነውና መፍትሔ የሆነውን ፀሎት እስክንረዳና እስክንፀልይ ነው፡፡ ነገር ግን በጣም የሚገርምና የሚደንቅ ነገር አንተም በፊት የሰማህ ወይም እራስ ተናግረህ የነበረ፣ ሁላችንም ያለንና የምናውቅ ቢሆንም ብዙውን ጊዜ ፀሎትን እንደመጨረሻ መፍትሔ ወይም ምንም ፀሎት ምንም ማድረግ የሚችል የማይመስለን ዝም ብሎ ፀሎት ነው፡፡ ያ ደግሞ የሚያሳየው ፀሎት ምንም ኃይል እንደሌለው ስለሚመስለን ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ ብዙ ሸክምና የከፋ ኑሮ በፀሎት ማስወገድና የቀላልና የእረፍት ኑሮ እንዳንኖር ተሸክመን እንዘምራለን፡፡ ነገር ግን ከዚህ ለመገላገል በፀሎት ለእግዚአብሔር በመናገር ከእርሱ ስንሰማና ስናዳምጠው እርሱ ስለሁሉ ነገሮች መፍትሔ እንዲሰጠን እንደመጨረሻ መፍትሔ ሳይሆን እንደመጀመሪያ ምርጫና ምላሽ (መፍትሔ) ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ፀሎት የሕይወትህ መጀመሪያ ምላሽ ይህ እንጂ የመጨረሻ መፍትሔ አይሁን፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon