የእግዚአብሔርን ሚስጥር መጠበቅ

የእግዚአብሔርን ሚስጥር መጠበቅ

አንተግንስትጸልይ፥ወደእልፍኝህግባመዝጊያህንምዘግተህበስውርላለውአባትህጸልይ፤በስውርየ ሚያይአባትህምበግልጥይከፍልሃል።(ማቴዎስ 6:6)

ለበርካታ አመታት ከእግዚአብሔር ጋር ባሳለፍኩት ልምምድ ሚስጥርን መጠበቅ ላይ ደካማ እነደሆንኩ ተገንዝቤያለሁ፡፡ የዛሬዉ ቃል በእኛና ለእግዚአብሔር የምንጸልየዉ ጸሎት ለሌሎች የተገለጠና ለታይታ መሆን እንደሌለበት ይናገራል፡፡ ከእግዚአብሔር መስማት እንፈልጋለን፣ ምንም እንዳልተናገረን ሲሰማን፣ ያንን ለሌሎች ለመንገር እንቸኩላለን፡፡ ምናልባትም በወቅቱ ትክክል ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን በእኛና በእግዚአብሔር መካከል ያለዉ ነገር በሚስጥር መጠበቅ ያለበት ጊዜ ይኖራል፡፡

ዮሴፍ አባቱና ወንድሞቹ አንድ ቀን እንደሚሰግዱለት በህልሙ ባየ ጊዜ፣ ምናልባትምይህንን ለነሱመናገሩ ልጅነትና ሞኝነት ነበር፡፡ ምናልባትም ይህ ሞኝነቱ እግዚአብሔር ሊያመጣዉ ወዳሰበዉ የሀላፊነት ቦታ በፊት ሊያዘጋጀዉ አስቦ ይሆናል፡፡ አብዛኛዉን ጊዜ ሚስጥርን ለመጠበቅ ፈቃደኛ አለመሆናችን አለመብሰላችንን ያሳያል፡፡ የዛሬዉ ቃል እንደሚናገረዉ፣ መናገርና በሚስጥር መጠበቅ ያሉብንን ነገሮች ማስተዋል ከቻልን፣ በህይወታችን የተገለጡትን የእግዚአበሔር ስጦታዎች የበለጠ ማየት እንችላለን ብዬ አስባለሁ፡፡

እግዚአብሔር እኛን ማመን በሚጀምርበት ጊዜ፣ ብዙ ነገሮችን እየገለጠልን ይሄዳል፡፡ እግዚአብሔር በልባችን አንድንጠብቀዉ የነገረንን ነገር እንድንገልጠዉ እሱ እስከሚፈቅድልን ጊዜ ድረስ በሚስጥር መጠበቅን እንለማመድ፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡ በስሜት ዉስጥ ስትሆንመናገር ስለምትፈልገዉ ነገርተጠንቀቅ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon