የዘለዓለም ፍሬ

የዘለዓለም ፍሬ

አብ እንደ ወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችሁ በፍቅሬ ኑሩ፡፡ ዮሐ 15÷9

ዴቭ (ባለቤቴ) ከቤታችን ደጅ ያለውን በጣም የሚያምር ያረጀ ዛፍ ለመከርከም ወይም ለመግረዝ የወሰነበትን ጊዜ ፈፅሞ አልረሳም፡፡ ብዙ ያረጁ ቅርንጫፎችና የተጣመሙ ነበሩ፡፡ እርሱ ባለሙያ አምጥቶ የመግረዝ (የመከርከም) ሥራውን በመሥራት እንዲያስተካክሉት ባለኝ ጊዜ ብዙም አልመሰለኝም ነበር፡፡ እቤት ስደርስና እነዚያን በመግረዣ መቀሳቸው እንጨቱን ሆን ብሎ በከንቱ እያበላሹት ነው ብዬ ደነገጥኩ፡፡

ዴቭ ‹‹እስከመጭው ዓመት እንደገና የበለጠ ያምራል፡፡›› አለኝ፡፡ እኔ ግን መጠበቅ አልቻልኩም፡፡

ለጥርስ መፋቅያ የሚሆኑ የለመለሙ ቅርንጫፎች ተገርዘው በመሬት ላይ ሞልተው ያሉትን እንኳ ማየት አልወደድኩም፡፡ ነገር ግን ዴቭ ትክክል ነበር፡፡ በሚቀጥለው ዓመት ዛፉ ከድሮ ይልቅ በጣም የሚያምር ኃይለኛ ንፋስን ለብዙ ዓመታት ብመጣ የሚቋቋም ሆነ ከድሮ ይልቅ ፍሬያማና ውጤታማ ሆነ፡፡ ይህ መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ለሚያደርገው ፍፁም የሆነ ምሣሌ ነው፡፡ የግዝረቱ ውጤት ውበት፣ ጥንካሬንና ፍሬያማነትን በሕይወታችን ያመጣል፡፡ ገላትያ ምዕራፍ 5 የሥጋ ሥራ የሆኑ የኃጥያት ዝርዝርና የመንፈስ ፍሬ የሆነውን የጻድቅ ሥራ ዝርዝር ይሰጠናል፡፡ ለመልካሙ ፍሬ መኖሪያ ይሆን ዘንድ በቀጣይነት የሥጋችን ግዝረት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ልክ እንደ የእኔ ዛፍ አንዳንዱድ ጊዜ በመወላገድ እና ምዘናችንን መጠበቅ ሲያቅተን እግዚአብሔር ጣልቃ ይገባና እንደገና ያበረታናል፡፡ እግዚአብሔር ስለሚጠነቀቅልንና ስለሚከታተለን እንዲሁም መሆን የሚገባንን በትልቅ የመግረዣ መቀሱ በቀጣይነት እንዲገርዝህና እጅግ በበለጠ የፍሬ መበልፀግ እንዲያስችልህ ጠይቀው፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- ቅጣት ጥሩ ስሜት አይሰጥም፡፡ ነገር ግን በኋላ ፍሬው የሚያስደስት ነው፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon