ዳንኤልም መልካም መንፈስ ስላለው ከአለቆችና ከመሳፍንት በለጠ ፤ ንጉሱም በመንግሥቱ ሁሉ ላይ ይሾመው ዘንድ አሰበ፡፡ – ዳንኤል 6፡3
ዳንኤል በመጽሀፍ ቅዱሳችን ውስጥ ‹‹ መልካም መንፈስ›› ያለበት ገላጭ ያለው ሰው ነው፡፡ ምንም ዓይት ዋጋ ቢያስከፍለው እንኳን ለእግዚአብሔር ክብር በመስጠት የኖረ ነው፡፡ ዳንኤል እግዚአብሔርን የሚወድ እና በመሰጠቱም ሳይዋልል ያገለገለ ነው፡፡ ይህንን በማድረጉም እግዚአብሄር ከንጉሱ ጋር አቀረበው በምድሪቱ ባሉ በመሪዎች ሁሉ ላይ ሹመትን አገኘ፡፡ የዳንኤል መሰጠት በእግዚአብሔር የተፈተ ነበር፡፡
መሪዎች አንደ ዳንኤል ያሉ የንጉሱ ሞገስ ያላቸው ሰዎችን አይወዱም ፡፡ ከዚህም የተነሳ አንገላቱት ፤ ንጉሱም ማንኛውም ሰው ለሰላሳ ቀናት ወደ አምላኩ እንዳይጸልይ የሚከለክል ትዕዛዝ እንዲፈረም አስደረጉ፡፡ የንጉስን ትዕዛዝ መተላለፍ ወደ አናብስት ጉድጓድ የሚያስጥል ወንጀል ሆነ፡፡
ዳንኤል ከንጉስ ትዕዛዝ ይልቅ ለእግዚብሔር መሰጠት ዋነኛ ትኩረቱ ነበር፡፡ ታሪኩን የምታውቁት ከሆነ በታሪኩ ውስጥ እግዚአብሔር በስተመጨረሻ እንዴት እንዳከበረው እና እንደጠበቀው ታያላችሁ፡፡
በዚህ ዓይነት መልካም መንፈስ እንድትኖሩ አበረታታችኋለሁ፡፡ በሕይወታችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር ቆራጦች ሁኑ፡፡ ይህን ስታደርጉ በሕይወት ያላችሁን እውነተኛ ዐላም ከግብ ታደርሳለችሁም ፤ እግዚአብሔርንም በነገር ሁሉ እንደ ዳንኤል ታከብራላችሁ፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
ጌታ ሆይ እንደ ዳንኤል ለላቀ ሕይወት ራሴን እሰጣለሁ ፡፡ በውስጤ መልካም መንፍስን አኑርልኝ፡፡ በሙሉ ልብ እንዳገለግልህም እርዳኝ፡፡