«ስለዚህም ኢየሱስ፦ የሰውን ልጅ ከፍ ከፍ ባደረጋችሁት ጊዜ እኔ እሆን ዘንድ አባቴም እንዳስተማረኝ እነዚህን እናገር ዘንድ እንጂ ከራሴ አንዳች እንዳላደርግ በዚያን ጊዜ ታውቃላችሁ» (ዮሐ. 8፡28)።
በተለያዩ አጋጣሚዎች እርሱ ከእኔ በተለያዩ ሁኔታዎች እኔ ምን እንዳደርግ እንደሚፈልግ በጸሎት እጠይቀው ነበር። እርሱም «ማድረግ የምትፈልገውን ማንኛውንም ነገር አድርግ» የሚል ምላሽ ሰጠኝ። እኔም እንደዚህ ዓይነት መልስ ለመጀመሪያ ጊዜ ስሰማ እንዲህ ዓይነት ነጻነት የሚሰጠኝ እግዚአብሔርን ማመን ፈርቼ ነበር። ነገር ግን አሁን በመንፈሳዊ ህይወታችን ይበልጥ እያደግንና እየበሰልን ስንሄድ የበለጠ ነጻነት እንደሚሰጠን አወቅሁ።
ስከዚህ ጉዳይ ሳስብ ሁሉን ማድረግ ያስፈለገኝ እውነት ስለልጆቼ በማሰብ ይህንን እውነት አረጋገጥኩ። ልጆቼ በዕድሜ ልጆችና ልምድ የሌላቸው በነበሩበት ጊዜ ሁሉንም ውሳኔ የምወስንላቸው እኔ ነበርኩ። እነርሱ ግን እያደጉና እየበሰሉ ሲመጡ እነርሱ ማድረግ የሚፈልጉትን ለራሳቸው እንዲወስኑና እንዲያደርጉ እፈቅድላቸው ነበር። እነርሱም ለብዙ ጊዜያት በባለቤቴ ዴቭና በእኔ ዙሪያ ስለነበሩ እነርሱ ይበልጥ ልባችንን ማወቅ ጀምረው ነበር። አሁን አራቱም ልጆቼ አድገዋል። እናም አብዛኛውን ጊዜ ማድረግ የሚፈልጉትን ነገር በራሳቸው ያደርጋሉ። እናም የተወሰነ ጊዜ አንዳንድ መገዳደሮች ቢኖሩም እነርሱ የእኛን ልብ ስለሚያውቁና በዚያው መንገድ ስለሚጓዙ ነው።
ለብዙ ዓመታት ከእግዚአብሔር ጋር ከተጓዝን በኋላ እኛ የእርሱን ልብ፣ ባህርይና መንገዱን ለማወቅ ቻልን። እኛም እርሱን ለመከተል በፍጹም ከተሰጠን እርሱ ትልቅ ነጻነት ሊሰጠን ይችላል፤ ምክንያቱም እኛ ከእርሱ ጋር «አንድ» ስለሆንን ነው። በመንፈሳዊ ህይወታችን ይበልጥ ስናድግ እግዚአብሔርን ይበልጥ ለማክበር እንፈልጋለን። እንዲሁም በምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ውስጥ የእርሱን ሀሳብ እናንጸባርቃለን። መንፈሳችን በመንፈስ ቅዱስ ሙሉ ይሆናልና የእኛ ፍላጎት ከእርሱ ፈቃድ ጋር የተዋሃደ ይሆናል።
በዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ኢየሱስ አባቱ ያስተማረውን ብቻ ያደርግና ይናገር እንደነበር እናነባለን። አንተም እንደዚህ ዓይነት «አንድነትን» ከእግዚአብሔር ጋር ይኖርህ ዘንድ ይህንን እንድትፈልግ አበረታታሃለሁ። በራስህ ምንም አታድርግ ወይም ከራስህ ፍላጎትና ጥንካሬ የሚነሳ ምንም ነገር አታድርግ፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር ባለህ እንደዚህ ዓይነት የጠበቀ ህብረት የሚሆነውን የፍላጎት አንድነት ደስተኛ ትሆናለህ።
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- የእግዚአብሔር ደስታ (ፍላጎት) የአንተ ደስታ (ፍላጎት) ይሁን።