ጌታ ሆይ እንዴት እንደምፀልይ አስተምረኝ

ጌታ ሆይ እንዴት እንደምፀልይ አስተምረኝ

እርሱም በአንድ ሥፍራ ይፀልይ ነበር በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ ጌታ ሆይ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንፀልይ ዘንድ አስተምረን አለው፡፡ ሉቃ 11÷1

በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ፍጹም ሕይወት ለዋጭ የሆነ ፀሎት ሰው የሚያደርገው ‹‹ጌታ ሆይ እንዴት እንደሚፀልይ አስተምረኝ›› ማለት የየቅል ነው፡፡ አየ ዝም ብሎ ስለፀሎት ብቻ ማወቅ በቂ አይደለም፡፡ እንዴት መፀለይ እንዳለብንም ማለት ለእግዚአብሔር መናገርና እርሱን ማዳመጥ እንደ ግለሰብ ከእርሱ ጋር ጥብቅ ኅብረት እንዳለሁ ሰው፣ ለሁሉም ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት መፍጠር ይፈልጋል፡፡ ምንም እንኳ ለሁሉም ሰው የሚያስፈልግ የፀሎት መመሪያ ቢኖርም እግዚአብሔር ግን እያንዳንዳችንን በተለየ መንገድ እኛን መገናኘትና የምንፈልገው ልዩ በሆነ የየራሳችን መንገድ በግላችን የፀሎት ልምምድ ነው፡፡ በሕይወቴ በፀሎት ትምህርታዊ ጉባኤ ብዙ ጊዜያት ተካፍያለሁ እንዲሁም ከሌሎች የሰማሁትን የፀሎት ልምምዳቸውን ከሌሎች እንደሰማሁት በሕይወቴ በተመሳሳይ የእነርሱን በመድገም ለመፀለይ እሞክር ነበር፡፡ በኋላ ግን ምንም እንኳ እግዚአብሔር ለእኔ የራሴ የሆነ የግሌ የፀሎት ዕቅድ እንዳለው ባውቅም ማለት እኔ ለእርሱ የምናገርበትና እርሱ ለእኔ የሚናርበት መንገድ በጣም የተሳካ መንገድ እና እኔም ያንን ምንና እንዴት እንደሆነ ለማወቅ ፈለኩ፡፡ እንዲህ በማለት ‹‹ጌታ ሆይ እንዴት እንደምፀልይ አስተምረኝ›› ፀሎት ጀመርኩ፡፡ እግዚአብሔርም ሃይልን በተሞላ መንገድ መለሰልኝ ከዚያም በጣም የሚያስደንቅ የፀሎት ሕይወት ለውጥ አየሁ፡፡

ከእግዚአብሔር ጋር በደስታ በጥልቀትና በቅርበት ሃይልን የተሞላ ሕብረት ማድረግ ከፈለክ እኔ እበረታታለሁ፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ እንዴት እንደምፀልይ አስተምረኝ›› በለው እርሱም ያደርገዋል፡፡ አንተም ወዲያውኑ ትልቅ ነፃነት ታገኛለህ፣ በፀሎትህም ውጤታማ ትሆናለህ፡፡ እግዚአብሔር ልዩ በሆነ መንገድ ይመራሃል፣ አዲስና በሚገርም እቅዱ ለአንተ ይሠራልሃል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- እግዚአብሔር ፀሎት እንዲያስተምርህ አድርግ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon