ፀሎትህ ኃይለኛና ረዥም መሆን አያስፈልገውም

ፀሎትህ ኃይለኛና ረዥም መሆን አያስፈልገውም

አህዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትፀልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድከሙ፡፡ ስለዚህ አትምሰሉአቸው ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና፡፡ ማቴ 6÷7-8

አንዱና ትልቁ የሰይጣን ውሸት ለሰዎች ስለፀሎት የምነግራቸው ረዥም ሰዓት መፀለይ እንዳለባቸው ነው፡፡ እርሱ በትክክል ፀለይኩ የምትለው ለረዥም ሰዓታት የፀለይክ እንደሆነ እንድታስብ ማድረግ ነው፡፡ ነገር ግን እኔ ከእግዚአብሔርም ቃል ሆነ ከልምምዴ እንደተረዳሁት ፀሎት ረዥም ሰዓት ስለተፀለየ ኃይለኛ አይሆንም፡፡ አጭርም በመሆኑ ኃይለኛ አይሆንም የፀሎታችን መርዘም በእግዚአብሔር ፊት ምንም ለውጥ አያመጣም፡፡ በአጠቃላይ ፀሎቱ በመንፈስ የመራቱ፣ ከልበ ሙሉነት በእውነተኛ እምነት መታጀቡ ነው ግድ ሊለን የሚገባን፡፡

ወቅት ፀሎታችን ኃይል እያጣ ይመጣል፡፡ እኔ ጠንከር አድርጌ መናገር የምፈልገው ፀሎን ማስረዘም በፍጹም በራሱ ምንም ስህተት የለውም፡፡ አስቀድሜ ለማንሳት እንደተሞከረው ከእግዚአብሔር ጋር ረዥም ሰዓት ወስዶ ኅብረት ማድረግና መፀለይ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ቅርበት ይወስናል፡፡ ነገር ግን ከመንፈስ ቅዱስ ምሪት ውጭ የሆነ የተወሰነ ሰዓት ለራሳችን በማስቀመጥ በፀሎት መታገል አለብን ብዬ አላምንም፡፡ እንደ ሥጋ ስራ ወይም እንደ ግዳጅ በሆነ ስሜት መደረግ የለበትም፡፡ ልዩ የሆነ ጉዳይ በሕይወታችን ገጥሞን ይሆናል፡፡ ነገር ግን ዝም ብለን ረዥም ጊዜ በመውሰድ ፀሎትን ማስረዘም የለብንም፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ፀሎትህ ከልብ የሆነና በእምነት የተሞላና በመንፈስ የተመራ ይሁን፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon