ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጥ

ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጥ

ባንዝልምበጊዜውእናጭዳለንናመልካምሥራንለመሥራትአንታክት።(ገላትያ 6:9)

ሰዎች የእግዚአብሔርን ድምጽ የማይሰሙበት ምክንያት ቶሎ ተስፋ መቁረጥ ዉስጥ ስለሚገቡ ነዉ፡፡ ጳዉሎስ እና ሲላስ ሌሊት በእስር ቤት ሆነዉም እንኳ ይዘምሩ ነበር(ሐዋርያት 16:25 ተመልከት)፡፡ አብዛኛዎቹሰዎች ተስፋ ቆርጠዉ ቶሎ ወደ እንቅልፍ ይሄዱ ይሆናል፡፡ መፈክራችን መሆን ያለበት “ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጥ፡፡” ነዉ፡፡

ምንም ይሁን ምን፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያላችሁን ንግግርና እሱን መጠበቅ ተስፋ ቆርጣችሁ አንዳታቋርጡ አበረታታችኋለሁ፡፡በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር ሆናችሁ ጊዜያችሁን አሳልፉ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ያለዉን ግንኙነት ማቋረጥ የማይፈልገዉን ሰዉ ሰይጣንም አያሸንፈዉም፡፡ አሱ የሚፈልገዉ እኛ ተስፋ ቆርጠን አንደዚህ አንድንል ነዉ፡፡

“የተሻለ ስራ በፍጹም ማግኘት አልችልም፡፡”
“ፈጽሞ ማግባት አልችልም”
“ከዕዳ ዉስጥ ፈጽሞ መዉጣት አልችልም፡፡”
“ዉፍረቴ ፈጽሞ አይቀንስም፡፡”

እንደዚህ አይነቶቹአመለካከቶችምንም እንደማንቀበል የሚያረጋግጡ ናቸዉ! ይሁን እንጂ “እግዚአብሔር በቃሉ ታማኝ ነዉ፣ በፍጹም ተስፋ አልቆርጥም፡፡” የሚለዉን አመለካከት መምረጥ ትችላለህ፡፡ሰዎች የጸሎታቸዉን መልስ ከማያገኙበት ምክንያቶች አንዱ ተስፋ መቁረጣቸዉ ነዉ፡፡ በጊዜዉ ማጨድ እንችላለን፣ ይሁን እንጂ ያጊዜ መች ነዉ? ጊዜዉ የጠየቅነዉን ለመቀበል ዝግጁ መሆናችንን እግዚአብሔር ሲያዉቅ ነዉ፡፡የኛ ተግባር መሆን ያለበት እስከዚያች ሰአት ድረስ ታማኝ ሆነን መጠበቅ ነዉ፡፡ መጸለይህን እንዲሁም
መታዘዝንም ቀጥልበት፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡ እግዚአብሔር ሁለተኛ እድል ይሰጠናል፣ ስለዚህ አዲስ ነገር ለመጀመር፣ ቀኑ ዛሬ ነዉ!

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon