መቁጠር አቁሙ

መቁጠር አቁሙ

ተገቢ ያልሆነ ነገር አያደርግም፤ ራስ ወዳድ አይደለም፤ አይበሳጭም፣ በደልን አይቈጥርም። – 1 ኛቆሮ 13፡5

ሁላችንም በሰዎች በሚደርስብን በደል ምክንያት በጣም እናዝናለን ፣ እንከፋለን ይሁን እንጅ በጣም ወሳኙና ትክክለኛው ነገር ይቅርታ ማድረግን መማር ነው፡፡ ይህ ደግሞ መንፈሳዊ ዕድገታችንንና ጥንካሬያችንን ይጨምርልናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ቢጎዳችሁ ለሚቀጥሉት አስር ዓመታት ያንን በቁጭት እያሰባችሁ ጉዳት ተሸክማችሁ መኖር የለባችሁም ምናልባትም ሌላኛው የጎዳችሁ ሰው እናንተን ስለመጉዳቱ እንኳ እረስቶት ይሆናል፡፡

ይቅርታ ባለማድረግ ስንመላለስ እየቆጠርን ነው ማለት ነው፡፡ በዚህም እራሳችንን ከሌላኛው ሰው የተሻልን አድርገን እያየን ነው ማለት ነው፡፡

እኔና ዴቭ በጋብቻ በነበርንባቸው በመጀመሪያዎቹ ዓመታት በምንጋጭበትና ቃላት በምንለዋወጥባቸው ጊዜ እኔ የቆዬ እና ብዙ የሰነበቱ መከፋቶችን እየመዘዝኩ አወጣቸዋለሁ፤ ዴቭ ግን ፈፅሞ እረስቷቸዋል፤ ከየት እንዳመጣኋቸው ሲጠይቀኝ በጭንቅላቴ ውስጥ እንደማከማቻቸው እንደምቆጥራቸውና ሌሎች ተጨማሪ ግጭቶችንም በዚያው ላይ እየጨመርኩ እንደምሄድ ነገርኩት ይህም በውስጤ ምሬትን እንደሚፈጥርብኝ አስረዳሁት፡፡

እግዚያብሔር ይመስገን አሁን በጣም የተሻለ አኗኗር መማር ችያለሁ፡፡ በእግዚያብሔር ፍቅር ስንመላለስ የደረሱብንን መጥፎ ነግሮች መቁጠር አቁመን በነፃነት መመላለስ እንጀምራለን፡፡ በመጎዳት እየተሰቃያችሁ ከሆነና ይቅርታ ማድረግ ካቃታችሁ እግዚያብሔርን እንዲረዳችሁ ለምኑት፤ ምሬታችሁን ዛሬውኑ እንዲሄድ አድርጉት፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚብሔር ሆይ የሰዎችን በደል በመቁጠር ይቅርታ ባለማድረግ ሕይወት መቀጠል አልፈልግም። ለአንተ እተዋለሁ ፣ መቁጠሬንም አቆማለሁ በአንተ ፍቅር እንድመላለስ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon