
የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ፣እርሱ ቀብቶኛልና፤ለታሰሩት መፈታትን፣ለታወሩትም ማየትን እንዳውጅ፣የተጨቆኑትን ነጻ እንዳወጣ…. – ሉቃ 4፡18
የመጣሁበት የጀርባ ታሪኬ የጥቃት እናም ያደኩበትም ቤተሰብ ፈራርሶ ነበር፡፡የልጅነት ዘመኔ በፍርሀት እና በስቃይ የተሞላ ነበር፡፡
ለክርስቶስ ለመኖር እና የክርስትናን የህይወት ዘይቤ ለመከተል እንደሚጥር ወጣት ወደፊቴ በየድሮው ታሪኬ እንደሚጨልም አምን ነበር፡፡እንዴት ነው እንደኔ አይነት የጀርባ ታሪክ ያለው ሰው ደህና ሊሆን የሚችለው? የማይሆን ነው!ብዬ አስብ ነበር፡፡
ኢየሱስ ያለው ግን የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው…ለታሰሩት ነጻነትን አውጅ ዘንድ ልኮኛል…ኢየሱስ የመጣው የእስር ቤት በሮችን ከፍቶ የታሰሩትን ነጻ ለማውጣት ነው፡፡
እግዚአብሔር ካለፈው ህይወቴ እስር ነጻ ሊያወጣኝ እንደሚፈልግ እስክረዳ ድረስ ምንም መሻሻል አላሳየሁም ነበር፡፡ካልፈቀድሁለት በስተቀር ያለፈው ህይወቴም ሆነ አሁን ያለሁበት ነገር ወደፊቴን እንደማይወስነው ማመን ነበረብኝ፡፡እግዚአብሔር በተአምራዊ መንገድ ነጻ እንዲያወጣኝ መፍቀድ ነበረብኝ፡፡
ምናልባት ዛሬያችሁን በአሉታዊ እና በሚያስደብር መንገድ የሚነካ የከፋ የኋላ ታሪክ ሊኖራችሁ ይችላል፡፡ነገር ግን በድፍረት እኔ እነግራችኋለሁ ወደፊታችሁ በኋላ ታሪካችሁ ወይም አሁን ባላችሁበት ሁኔታ ሊወሰን አይገባውም!ያለፈ ህይወታችሁን ሰንሰለት እግዚአብሔር ይስበርላችሁ፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ካለፈው ታሪኬ በላይ አንተ ይበልጥ ሀይለኛ እንደሆንክ አምናለሁ፡፡የሰጠኸኝን ነጻነት በመቀበል ለእኔ ያሉህን እቅዶች መኖር እፈልጋለሁ፡፡