
ቃሌ እንደእሳት(ፈተናውን ማለፍ ያልቻለውን ሁሉ የሚበላ)፣ድንጋይንም እንደሚያደቅ መዶሻ (በጣም ደረቅ ተቃውሞን)አይደለምን ላል እግዚአብሔር፡፡ – ኤር 23፡29
“መናዘዝ” የሚለውን ቃል ስትሰሙ ብዙ ጊዜ የምታስቡት ምንድነው?ብዙ ጊዜ ሰዎች መጀመሪያ የሚመጣላቸው የተሳሳተ ነገር እንደሰሩ እንዲያምኑ የሚያስገድድ አሉታዊ ትርጉሙን ነው፡፡ነገር ግን ድምጽን አውጥቶ በመናዘዝ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ስንስማማ ውጤቱ ሁሌም አዎንታዊ ነው፡፡
አንድ ከእኔ ጋር የሚሰራ ሰው ጎሊያድን አፋችንን ዘግተን ማሸነፍ አንችልም ይላል፡፡ዳዊት ከግዙፉ ጎሊያድ ጋር ጦርነትን ለማድረግ ሲዘጋጅ የጦርነቱ መጨረሻ ይሆናል ብሎ የሚያምንበትን፡እግዚአብሔር ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል…(1ኛ ሳሙ.17፡46) ጮክ ብሎ እየተናዘዘ ነው ወደ እርሱ የሮጠው፡፡
ይሄ በህይወታችን ጠላቶቻችንን እንዴት መቅረብ እንዳለብን ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡የግድ አፋችንን ከፍተን የእግዚአብሔር ቃል መናገር አለብን፡፡
በየቀኑ ጮክ ብላችሁ የእግዚአብሔርን ቃል እንድትናዘዙ በጣም አበረታታችኋለሁ፡፡በእያንዳንዱ ጊዜ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይስማማ ሀሳብ ወደ አዕምሯችሁ ሲመጣ የእሱን ቃል እውነታ ጮክ ብላችሁ ተናዘዙት እና የቃሉ ሀይል ውሸቱን ሲያሸንፈው ታያላችሁ፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ቃልህ ሀይለኛ ነው…ምንም ሊቋቋመው አይችልም፡፡ሁልጊዜም ራሴን በከባድ ሁኔታ ውስጥ ሳገኘው ቃልህን ጮክ ብዬ እንዳውጅ አሳስበኝ፡፡